ከምትናገረው በላይ አድምጥ

ከምትናገረው በላይ አድምጥ

እውቀት ያለው ቃሉን ይርቃል ፤ አስተዋይም ሰው ቀዝቃዛ መንፈስ አለው። (ምሳሌ 17:27)

በዚህ ጥሞና ጊዜ ማስታወሻ ውስጥ እንደተናገርነው ከእግዚአብሄር ለመስማት በምናደርገው ጥረት ማዳመጥ እንድንችል ራሳችንን ማስተማር አለብን። አንዳንድ ጊዜ በጣም ተናጋሪዎች ስለሆንን በቀላሉ እግዚአብሔር ሊናገር የፈለገውን መስማት አንችልም። ካለመሰማታችን የተነሳ ሰዎች የሚሉንን ጠቃሚ ነገሮችም እንዲሁ ልናጣ እንችላለን።

የመረጋጋትን እና ዝም የማለትን ስነ-ስርዓት ከተማርን፣ እግዚአብሔር ሊናገረን የሚፈልገውን ነገር እንሰማለን። ልጄ ሳንድራ በቅርቡ ከጸለየች በኋላ አንድ ደቂቃ ያህል ቁጭ ብላ ቀኑን ከመጀመሯ በፊት ሊነግራት የሚፈልገው ነገር ካለ እግዚአብሔርን እንደጠየቀችው ተናገረች። በቀላሉ “ሂጂ፤ እኔ ካንቺ ጋር ነኝ” እንዳላት ተሰማት። በዚያ ሀሳብ ተጽናናንታ ነበር፣ በተለይም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ አንዳንድ ያልተጠበቁ መጥፎ ዜናዎችን መቋቋም ነበረባት።

ካላዳመጥን አንሰማም፤እግዚአብሔር በመደበኛነት እንዲናገርህ ዕድል ስጠው። በምትጸልይበት ጊዜ ሁሉንም ንግግር ማድረግ አይጠበቅብህም። ቃላትህን መቆጠብ እና እንደ ጥበበኛ የእግዚአብሔር ሰው ወይም ሴት ልትቆጠር ትችላለህ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እአንድ አፍ እና ሁለት ጆሮዎች አሉህ፣ ስለዚህ ያ ማለት ደግሞ እግዚአብሔር የምትናገረውን ያህል ሁለት እጥፍ እንድታዳምጥ ይፈልጋል ማለት ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon