ከባዱን ነገር ለእግዚያብሔር ተውለት

ከባዱን ነገር ለእግዚያብሔር ተውለት

እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በእርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና። – ዮሐ 15፡5

በጣም ከተማርኳቸው ጠቃሚ ትምህርቶች መካከል ዋነኛው ከባዱን ነገር ለእግዚያብሔር መተው ነው፡፡ በጣም በርካታ ጊዜያት ነገሮችን በራሳችን ብልሃትና ችሎታ ለመፍታት እንታገላለን ይሁንና ውጤታሞች ግን አይደለንም፡፡

እራሳችን ለራሳችን በቂ መስሎ ሊታየን ይችላል ነገርግን የእግዚያብሔር ፀጋና ማስቻል ሊቸረን ይገባል። ጉልበትና ቁርጠኝነት ነገሮችን ሊያስጀምሩን ይችላሉ ነገርግን አብዘሃኛውን ጊዜ ዘላቂ አይደሉም ፣ በችግር መሃልም ጥለውን ሊሄዱ ይችላሉ።

እግዚያብሔር በእያንዳንዱ ጉዳያችን ጣልቃ እንዲገባ ማድረግ ፤ በኢየሱስ በኩል የሰጠንን ደስታ መደሰት መማር አለብን፡፡ ኢየሱስም አለ፤ ማቲ 11፡28 “እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።“

ከእግዚያብሔር ውጭ ምንም ነገር ልናደርግ እንዳንችል ሆነን ተሰርተናል፤ ከእርሱ ጋር ሆነን የማንሻገረውና የማንሰብረው ክፉ ልማድና ጠባይ የለም፡፡ ኢየሱስ ከገጠማችሁ ከየትኛውም ችግር በላይ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ እኔ ከአንተ ውጭ ምንም ማድረግ አልችልም ስለዚህ በህይወቴ ክፍሎች ሁሉ ላይ እሾምሃለሁ ከባዱን ነገር እንድታደረገው እፈቅድልሃለሁ ሁሌም እክተልሃለሁ እደገፍብሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon