በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም። – ዕብራዊያን 4፡15
ተጎድተን ከሆነ ፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ከሆንን ፣ በብስጭት እና በግራ መጋባት ውስጥ ከሆንን ትክክለኛ ምርጫን ማድረግ ጠቃሚ ነው የፈለገ ከባድ ቢሆንም፡፡ በጫና ውስጥ ስንሆን በተፈጥሯችን ቀላሉን መንገድ የመውሰድ ባህሪ አለን፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነ ትክክለኛውን ምርጫ ማድረጋችን ትልቅ ልዩነትን ያደረጋል፡፡ ምክንያቱም በሕይወት ትክክለኛ ውጤቶችን ለማጨድ ፤ ማድረግ ያለብን ነገር ጥሩ ባይሰማን እንኳን ትክክለኛውን ነገር ማድረግ አለበን፡፡
በጣም የሚደንቀኝ ኢየሱስ ምን እንደሚሰማን ማወቁ ነው፡፡ ኢየሱስ ሰው በሆነ ጊዜ እኛን በሚያስቸግሩን መከራዎች እና ተግዳሮቶች ሁሉ አልፎባቸዋል፡፡ እርሱ ተስፋ መቁረጥ ተሰምቶት እንዲሁም ቀላሉን መንገድ ለመውሰድም አስቦ ነበር ይሁን እንጂ ተግዳሮቶቹን ሁሉ አሸንፎ ጠንካራ ምርጫዎችን አድርጓል፡፡
ቁርጠኝነታችን ሲዳከም እና ሲጠወልግ ፤ የምናገለግለው አምላክ የምናልፈበትን መንገድ እንደሚያውቅ በድፍረት እናውቃለን፡፡ ጠንካራ ውሳኔዎችን ለብቻችን እንዳንወስን እና በእርሱ እርዳታ ማድረግ የምንችልበት ጸጋ ሊሰጠን እና ሊደግፈን ይፈልጋል፡፡ ተስፋ በመቁረጥ እና በጭንቀት ጠርዝ ላይ ራሳችንን ስናገኝ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዳለ እናስታውስ ይህንንም እንረዳ፡፡ በእርሱ ውስጥ ጥንካሬን እና ጠንካራ ምርጫ ማድረግ መቻልን እናግኝ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ሁሉን ነገር መረዳት ስለምትችል ደስተኛ ነኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ተግዳሮቶችን መጋፈጥ በማንችልበት ሁኔታ ውስጥ አንኳ በአንተ ውስጥ ምን መምረጥ እንደምችል የሚያበረታኝ ብርታት አገኛለሁ፡፡