ካላችሁበት ሆናችሁ ተመልከቱ

ካላችሁበት ሆናችሁ ተመልከቱ

ሎጥ ከተለየው በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤”ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ ወደ ሰሜን እና ወደ ደቡብ፣ወደ ምስራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት…”-ዘፍ.13፡14

ህይወት ሁልጊዜ እንደአዲስ መጀመር ወዳለብን ቦታ የሚያደርሰን የራሱ የሆነ መንገድ አለው፡፡

በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ አብራም የወንድሙ ልጅ ሎጥ በአከባቢው ያለውን መልካም ምድር መርጦ ብዙም የማይፈለገውን ምድር ለአብራም ሲተውለት አብራም ራሱን ያገኘው በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡እግዚአብሔር ግን አብራምን አልተወውም፡፡ይልቁንም ለአብራም አዲስን ራዕይ አሳይቶ ሰጠው፡፡

ከሎጥ ጋር ከተለያዩ በኋላ እግዚአብሔር ለአብራም የተናገረውን ነገር እወደዋለሁ፡፡”ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ…ተመልከት”

በጣም የሚነካኝ ሀረግ ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ…ተመልከት፡፡ይሄ የአዲስ ጅማሮ ነጥብ…አዲስ መነሻ ነው፡፡እግዚአብሔር ራሱ አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ወዳለ ስፍራ ያመጣናል፡፡

ምናልባትም አሁን እሱ ስፍራ ላይ ሊሆን ይችላል ያላችሁት፡፡ከመጥፎ ልምድ ለመውጣት ወይም የጠፋውን ህልማችሁን ለመመለስ ትፈልጉ ይሆናል፡፡ገቢያችሁን በሚገባ መቆጣጠር፣የራሳችሁን ስራ መጀመር፣መጽሀፍ መጻፍ…ምንም ነገር ቢሆን እግዚአብሔር አሁን እንድትጀምሩት እየነገራችሁ ይሆናል፡፡ይህ አዲስ ጅማሬያችሁ ሊሆን ይችላል!

እግዚአብሔር አብራምን ከዛ ስፍራ ሆኖ እንዲመለከት ከነገረው በኋላ የነገረው ሌላ ነገር “እንግዲህ ምድሪቷን ስለምሰጥህ ተነሣ፤በርዝመቷም፣በስፋቷም ተመላለስባት፡፡”ብሎ ነው፡፡ዘፍ.13፡17
እግዚአብሔር አሁን ተነስታችሁ ህልማችሁን…ስራችሁን…ህይወታችሁን እንድትኖሩ እየነገራችሁ ይሆናል ሰጥቷችኋልና፡፡የእናንተ ድርሻ መራመድ ነው፡፡

ማድረግ ያለባችሁን አድርጉ፡፡ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡ጊዜን ሊወስድ ይችላል፡፡ነገር ግን እግዚአብሔርን እመኑትና ምንም ነገር ቢሆን አድርጉት፡፡
አሁን ካላችሁበት ሆናችሁ ተመልከቱ-እና ሂዱ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ባለፈው ያጋጠመኝ ነገር ምንም ሆነ ምን አሁን ካለሁበት አሻግሬ እንዳይ እርዳኝ፡፡ለእኔ ስላለህ አዲስ ጅማሮ አመሰግናለሁ፡፡ለእኔ ያለህን ጥሪ በድፍረት ገብቼ እሄድበታለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon