
ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል . . . . ዳን 2 21
ከዓመታት በፊት በቤተክርስቲያን ውስጥ ደስ በሚያሰኝ ሥራ ላይ ነበርኩ፡፡ አገልግሎቴም በጣም አድጎ ነበር፡፡ ቋሚ ክፍያ ነበረኝ የፈለኩትን የማድረግ ብዙ ዕድሎችና አጋጣሚዎች ነበሩኝ፡፡ ነገር ግን አንድ ወቅት የእግዚአብሔር ድምፅ አሁን ያለሁበትን ሥራ ትቼ በመውጣት አገልግሎቴን ወደ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ እንዳስፋፋ ሲነገረኝ ሰማው፡፡ አሁን ያለሁበት የሕይወት ሁኔታ አልቆአል፡፡ ከዚህ ቦታ ካንቺ ጋር ያለኝን ጉዳይ ጨርሻለሁ አለኝ፡፡
እግዚአብሔር እንደተናገረኝ ከልቤ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን የተደባለቀ ስሜትና ፍርሃት ካለሁበት ሁኔታ ወጥቼ የግሌን አገልግሎት ስለመጀመር ግራ አጋባኝ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ ማለት የማውቀውን ለማድረግ የሚመጣው አደጋ እፈራለሁ፡፡ ነገር ግን ደግሞ ስህተት ሰርቼ ያለኝን እንዳላጣም እፈራለሁ፡፡ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ታላቅ እርምጃ ወደማላውቀው አገር ለመውሰድም ሆነ ለመሄድ ፈራው፡፡
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ስለጨረሰ ጉዳይ እኛ ነገሩን አንጠልጥለን እንይዘዋለን፡፡ መንፈሴ እርምጃ እንዲወስድ ይፈልጋል፡፡ ሥጋዬ ደግሞ እንዲቆይ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ለቅቄ እንውጣ ከምፈልገው ቦታ ብዙ የክብር ጥበቃዎች አሉኝ፡፡ እኔም ቦታውን ለቅቄ ለመውጣት አልፈልግም ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን እርሱን ታዝዤ በመውጣት በዓለም አቀፍ ባለኝ አገልግሎት አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር ነገሮችን ይለውጣል፡፡ ስለዚህ እኛም እርሱ ሲያዘንና ሲመራን ልንታዘዘውና ሊመራን ያስፈልጋል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔርን ድምፅ ሲመራህ አድምጥ ተከተለው በሕይወትህ እንዲመጣ ከፈለክ፡፡