ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፡፡ ያዕ፡ 4:8

ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር የመቅረብን ዋጋ ሊተምን የሚችል የለም፡፡ ማንም ሰው ከመሬት ተነስቶ እንዲሁ ለመንፈሣዊ ዕድገት የሚሆን ጊዜ ማጥፋት አይችልም፡፡ እግዚአብሔር ጊዜአችንን ሁሉ አልጠየቀንም፡፡ እርሱ ብዙውን ጊዜ ከእኛ የሚፈልገው ለእኛ መንፈሣዊ ነገር የማይመስለን ነገር እንድናደርግ ወይም እንድንሰራው ነው፡፡

እርሱ ሲፈጥረን እኛ አካል፣ ነፍስ (አእምሮ፣ ፈቃድ፣ ስሜት) እና መንፈስ እንዲኖረን አድርጎ ነው፡፡ እርሱ ከእኛ የምንፈልገው ለእነዚህ ሁሉ ጥንቃቄና እንክብካቤ እንድናደርግ ነው፡፡

አካላችንን ለማሰልጠንና ለነፍሳችን ጥበቃና ጥንቃቄ ለማድረግ ጊዜና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስሜታችን ቁጥጥር፣ ደስታና መዝናናት እንዲሁም ከሰዎች ጋር አብሮ በመሆን መደሰትን ኅብረትን ይፈልጋል፡፡ አእምሮአችን በየቀኑ ማደግና መታደስ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ እኛ ከተፈጥሮአችን መንፈሳዊ ይዘት ስላለን ትኩረት ይፈልጋል፡፡ ሚዛናዊና ጤነኛ ለመሆን ጊዜ ወስደን ለሁለንተናዊ ተፈጥሮአችን ጥንቃቄና ጥበቃ ልናደርግላቸው ይገባናል፡፡

እንደ እኔ እምነት ጠቅላላ የሕይወታችንን ጉዳይ የሚወስነው የእግዚአብሔር ጋር የምናሳልፈው ጊዜና ቀረቤታ ነው፡፡ እኛ ብዙን ጊዜ እግዚአብሔር ለመፈለግ ጊዜ የለንም፡፡ እኛ ብዙ ጊዜአችንን የምናሳልፈው በሕይወታችን በጣም አስፈላጊ በምንል ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ብናውቅም ብዙ ጊዜአችንን የምናጠፋው ጥፋቶችን በመቃወምና በመታገል ላይ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን አውቀን ብንሰማው ጊዜ አግኝተን ነገሮችን ለመሥራት በቻልን ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በራስህ ቀመር ውስጥ ገብቶ እንዲሠራ አትልፋ ይልቅስ ቀመርህን በእርሱ ጊዜ ውስጥ ለማስገባት ትጋ፡፡ እግዚአብሔርን ፈልጎ ማግኘት የረጅም ጊዜ ትግል ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ ቶሎ ብሎ የትርፍህ ፍሬ ባይደርስም ባለህ ጊዜና ፈቃድህ እርሱን ለማክበር በመወሰን በትዕግሥት ተጠባበቅ በጊዜና በሰዓቱ ፍሬህን ታገኛለህ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ላንተ፡- ልክ እንደ አካላዊ ልምምድ መንፈሳዊ ልምምድም በየጊዜው ልምምድ ይፈልጋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon