በነገር ሁሉ በፀሎትና በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ፡፡ ፊል፡ 4 6
በሕይወቴ ከእግዚአብሔር ጋር በነበረኝ ጉዞ ውስጥ እርሱ ከእኔ ጋር የሚሞግተው ለማለት የፈለኩትን ነገር በጥቂት ቃላት ለመግለፅ እንደምችል ነበር፡፡ እኔ በሕይወቴ በፀሎት ጊዜ ብዙ የመናገር መጥፎ ባሕሪ ነበረኝ፡፡ የተሳሳተ የፀሎት ግምት ስለነበረኝ አጭር ፀሎት ጥሩና ውጤታማ ስለማይመስለኝ ነበር እደጋግም የነበርኩት፡፡ በእርግጥ ረዥም ፀሎቶች በመሠረቱ ጥሩ ናቸው እውነተኛና አስፈላጊ እስከሆኑ ድረስ፡፡
እግዚአብሔር የእኔን ፀሎቶችና ጥያቄዎች በተቻለ መጠን በጥቂት ቃላት እንዲሆኑ ሲሞግተኝ በነበረ ጊዜ የእኔ ጥያቄ እጥር ምጥን ያለች ሆነ ወደ ዋና ነገሩ ያተኮረ ሆኖ በእርሱ ፊት በፀሎት በቀላሉ ከተናገርኩ በኃላ ለጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ የፀሎት አርዕሥት ከማለፉ በፊት እንዲቆይ ጠየቀኝ፡፡ ከዚያ በዚያው ሰዓት በሕይወቴ የምገርም ኃይል ከዚህ በፊት ያልተለመድኩት የፀሎት ኃይል በሕይወቴ ተጨመረ፡፡ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ዓይነት መንገድ ስፀልይ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ተለማምጄ አላውቅም፡፡
እኔ ከተማርኩት በጣም ኃይለኛና ውጤታማ ፀሎቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ‹‹ጌታ ሆይ ተመስገን››፣ ‹‹ኦ ጌታሆይ ያንተ ጥበብ ያስፈልገኛል››፣ ‹‹ጌታ ሆይ ወደፊት እንዲቀጥል ኃይል ሰጠኝ›› ወይም ‹‹እየሱስ እወድሃለሁ›› ‹‹ጌታ ሆይ ተያለህ; የሚሉ ፀሎቶች ናቸው፡፡ ጌታ በእኛ ጉዳይ ጣልቃ እንድገባ በጥቂት ቃላት ስንፀልይ ሕይወታችን ከመንግሥተ ሰማይ ጋር ይቆራኛል፡፡ የፀሎታችን እርዝማኔ ሳይሆን ውጤታማ የሚያደርገው የእኛ መታመንና እምነት ነው፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንቴ፡- በፀሎትም እንኳ ብሆን ጥራት ከብዛት እጅግ ይበልጣል፡፡