ወዳጅነት ድፍረትን ይሰጣል

ወዳጅነት ድፍረትን ይሰጣል

እንግዲህ ምህረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳን ፀጋ እንድናገኝ ወደ ፀጋው ዙፋን በእምነት (በድፍረት እንቅረብ) ፡፡ ዕብ 4 ÷ 16

ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረትና ወዳጅነት እየገባን ሲመጣ ፀሎታችን የበለጠ በመንፈስ የተመራ፣ እምነትን የተሞላና እርግጠኛ እየሆነ ይመጣል፡፡ ጌታ ኢየሱስ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ላይ ያለውን ታሪክ የነገራቸው ‹‹የጌታ ፀሎት›› እንዲሰጣቸው እንረዳለን፡፡ እንዲሁም አላቸው፡፡ ከእናተ ማናቸውም ወዳጅ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን ያም ከውስጥ መልሶ አታድክመኝ አሁን ደጁ ተቆልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን; እላችኋለሁ ወዳጅ ስለሆነ ስለሆነ ተነስቶ ባይሰጠው እንኳ ስለነዘነዘው ተነሥቶ የምፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል፡፡ ሉቃ 11፡ 5-8

አስተውል ያሰው እንጀራን ፈልጎ የለመነውና ማግኘት የቻለው ያለዕፍረት ስለነዘነዘውና እረፍት ስለነሣው ብቻ ነው፡፡ እኛም ከባልንጀራችን ጋር ያለ እፍረት ስንፀና ኅብረታችን ጠንካራ ይሆናል፡፡ ኅብረታችንም በጠነከረ መጠን እያደገና እየጎልበት እንደሄድ ሁሉ ከእግዚአብሔርም ጋር ኅብረታችን በጠነከረ መጠን በእርሱ የመተማመናችንም ድፍረትም ይጠነክራል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ወደ እግዚአብሔር ስትፀልይ ልክ ከቅርብ ወዳጅህ ጋር በምታደርገው ቅርበትና ስሜት ጥልቅ ግንኙነት መሆን አለበት፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon