የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ

የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ

…ሁሉም በመንፈስ ቅዱ ተሞሉ፤የእግዚአብሔርንም ቃል በድፍረት ተናገሩ፡፡ – ሐዋ 4፡31

በጣም ብዙ ዳግም ተወልደው በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ለእርሱ እውቅናን በመስጠት እና በየዕለቱ እርሱን በመከተል በእግዚአብሔር መንፈስ ሙሉ ሆኖ መቆየት ምን እንደሆነ የማያውቁ ደስተኛ ያልሆኑ አማኞች አሉ፡፡መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ቢኖርም በየዕለት ተዕለት ህይወታቸው ማረጋገጫው እንዲታይ አልፈቀዱለትም፡፡

አንድ ብርጭቆ ውስጥ እስከሚችለው ድረስ ሳይሞሉ ውሀ መጨመር ይቻላል፡፡በተመሳሳይ መንገድ ዳግም ስንወለድ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን አለ ነገር ግን ጢም ብለን ላንሞላ እና የሀይሉም መገለጫ በህይወታችን ላይታይ ይችላል፡፡

ሐዋ 4፡31 ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ሲሞሉ የእግዚአብሔርን ቃል በድፍረት እንደሚናገሩ ይነግረናል፡፡

ሰዎች ከዕለት ተዕለት ህይወታቸው ውስጥ አውጥተውት የራሳቸውን የሀይማኖት ቀመር እርሱን ለማባበል ሲጠቀሙ እግዚአብሔር ደስ አይለውም፡፡ይልቁንስ በመንፈስ የተሞላ የነጻነትእና የድፍረት ኑሮ እንድንኖር ነው የሚፈልገው፡፡

በህይወታችሁ በየትኛውም አቅጣጫ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በነጻነት እንዲሰራ እንድትፈቅዱለት እጠይቃችኋለሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በየዕለቱ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት እፈልጋለሁ፡፡በእያንዳንዱ የህይወቴ ቀናት በመንፈስ ቅዱስ ላገኝ በምችለው ነጻነት እና ድፍረት እንድኖር እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon