የመገዛትዝንባሌያችን

የመገዛትዝንባሌያችን

ሕግን) [የሰዉና የእግዚአበሔር] ከመስማትጆሮውንየሚመልስጸሎቱአስጸያፊ[በእግዚአበሔር ፊት]ናት።(ምሳሌ 28:9)

የዛሬዉ ቃል ስለጸሎቶቻችንናለሚገባዉ ስልጣንበሚገባ ካልታዘዝን በእግዚአብሔር ላይ እያመጽን እነደሆነ የሚያስደነግጥ ነገር ይነግረናል፡፡
ስህተቶቻችንን እያረምን ካልሄድን በቀላሉ ማደግና መብሰል አንችልም፡፡ የአንድን ድርጅት ህግ፣ የትራፊክንም ህግ ወይም ማንኛዉንም ስልጣን ካላከበርን፣ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ዉስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ አመጽ ከህይወታችንና ከማንነታችን ልናስወግደዉ የሚገባ ነገር ነዉ! ለምን? ምክንያቱም በምድር ላይ ያለዉን ስልጣን ካልተቀበልን፣ የእግዚአብሔርንም ስልጣን አንቀበልም ማለት ነዉ፡፡ ይህ አለመታዘዝ ሲሆን ዉጤት ያለዉን ጸሎት እንዳንጸልይ ያደርጋል፡፡

እግዚአብሔር የራሴን አገልግሎት እንድጀምር ሳይፈቅድልኝ በፊት ለአያሌ አመታት ለሌላ ሰዉ በተሰጠዉ አገልግሎት ዉስጥ እንዳገለግል አስቀመጠኝ፡፡ ለአንድ ስልጣን እንዴት መገዛት እንዳለብኝ መማር ነበረብኝ፡፡ ያ ለኔ ቀላል አልነበረም፡፡ ሁልጊዜ ከሚወሰኑ ዉሳኔዎች ጋር አልስማማም ነበር፣ በአግባቡም መብቴ እንደተጠበቀ አይሰማኝም ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ካስተማረኝ ነገሮች ማካከል አንዱ እንዴት ለስልጣን መገዛት እንዳለብን ካላወቅን በስተቀር በስልጣን ስር መገዛትን እንደማንፈልግ ነዉ፡፡

በስራቦታ ስለደሞዝ ጭማሪ ወይምየስራ እድገት ትፈልግ ይሆናል፣ ከዚህ ሌላ ስለአለቃህ በተደጋጋሚ በሚስጥር ታወራለህ፡፡ ይህ አንዱ የአመጽ አይነት ሲሆን እድገትህ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣ ነዉ፡፡ ለመገዛት ፈቃደኝነት ይኑርህ፣ የጸሎትህን መልስ ታገኛለህ የእግዚአብሔርንም ድምጽ የበለጠ በግልጽ ትረዳለህ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ በህይወት እንድታደርጋቸዉ የምትጠየቃቸዉነገሮች ሁሉ አግባብነት ያላቸዉ ነገሮች ላይሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ላይ እግዚአብሔር ፍትህን ያመጣልሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon