የሚመቸንን ብቻ መርጦ መስማት አይፈቀድም

የሚመቸንን ብቻ መርጦ መስማት አይፈቀድም

«ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀጥራል» (ዕብ.4፡7)።

በአንድ የህይወታችን ገጽታ ወይም ክፍል የእግዚአብሄርን ድምጽ ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆንን፣ ብዙውን ጊዜ በሌሎችም የህይወታችን ክፍሎች ላይ እግዚአብሔር የሚናገረውን ለመስማት አንችልም። አንዳንድ ጊዜ እኛ መስማት የምንፈልገው ብቻ መርጠን እንሰማለን፣ ይህ ዓይነት አሰማም «የሚመቸንን ብቻ መርጦ መስማት» ተብሎ ይጠራል። ይህ በሚሆንበት ጊዜ በመጨረሻ ሰዎች እግዚአብሔርን መስማት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ። ይህ ደግሞ እጅግ ክፉ ነገር ነው። እውነታው ግን እግዚአብሔር ይናገራቸዋል እነርሱ ግን ለእርሱ ምላሽ ከመስጠት ወድቀው ይገኛሉ።

ይህንን እውነት ለማብራራት አንድ ምሳሌ ልጠቀም። አንድ ሴት እግዚአብሔር በህይወቷ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ አቅጣጫ እንዲሰጣት እንደጸለየች ነገረችኝ። እርሷ እንድታደርግ እርሱ ከእርሷ የሚፈልገው ከወራት በፊት ከእህቷ ጋር የነበራት ጥል ይቅር እንድትላት ነበር። ይህቺ ሴት ግን ይቅርታ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነችም፣ ወዲያው ጸሎት አቆመች። መልሳ ደግሞ ለሌላ ጉዳይ የጌታን ፊት ስትፈልግ፣ አሁንም መልሳ በልቧ የምትሰማ «በመጀመሪያ እህትሽን ይቅር በይ» የሚል ድምጽ ነበር።

ከሁለት ዓመት በኋላ ሁልጊዜ ስለ አዲስ ወቅታዊ የህይወቷ ሁኔታዎች ከእግዚአብሔር ምሪትን ስትጠይቅ እርሱ አሁንም በዝግታ ድምጽ ይቅርታ እንድታድርግ ያስታውሳታል። በመጨረሻም እርሷ ያረጋገጠችው ነገር ቢኖር ካልታዘዘች በስተቀር ከዚህ አሰልቺ ህይወት ለመውጣትና በመንፈሳዊ ህይወት ለማደግ እንደማይቻል ነው። ከዚያም እንዲህ ብላ ጸለየች «ጌታ ሆይ እህቴን ይቅር ማለት እንድችል ኃይልህን ስጠኝ»። ወዲያውኑ ስለእህቷ ያላት አመለካከት ከዚህ ቀደም ያልነበራት ብዙ መረዳቶች መረዳት ጀመረች። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከእህቷጋር ያላት ግንኙነት ታደሰና ከዚህ ቀደም ከነበረው በላይ የጠነከረ ህብረት አገኙ።

እኛም በትክክል እግዚአብሔርን መስማት የምንፈልግ ከሆነ እርሱ ሊናገረን የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለመስማት ራሳችንን ክፍት ወይም የተዘጋጀን መሆንና ለሚናገረውም ምለሽ መስጠት አለብን። እኔ አሁን ዛሬ የማደፋፍርህ ነገር እርሱን እንድትሰማውና እንድትታዘዘው ነው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ በአንድ የተወሰነ የህይወትህ ክፍል ብቻ ላይ የሚመችህን መርጠህ የመስማት ልምድ አለህን? የእግዚአብሔርን በሁለንተናህ ለመስማት ፈቃደኛ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon