የሚረብሹ ነገሮችን ማስወገድ

የሚረብሹ ነገሮችን ማስወገድ

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግስትና ጽድቁን እሹ፤እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡ – ማቴ 6፡33

አንዱ ሰይጣንን በጣም የሚያስደስተው መሳሪያ መረበሽ ነው፡፡በአለም ባሉ ሌሎች ነገሮች ከተያዝን በእርግጠኝነት ከእግዚአብሔር ጋር ማሳለፍ ያለብንን ጊዜ እንደምንረሳው ያውቃል፡፡

እግዚአብሔር እኛን ታማኝ አድርጎ ለመጠበቅ እና ከእርሱ ጋር የቅርብ ህብረት እና ግንኙነት እንዲኖረን አንዳንዴ እሱን ከእኛ እንድንለያይ የሚያደርጉንን ነገሮች ቢያመንም እንድናስወግድ ይፈልጋል፡፡

ለምሳሌ ስራችን ወይም ለገንዘብ ያለን መሻት ወይም በህብረተሰቡ ውስጥ የሚኖረን ከፍ ያለ ቦታ ለእኛ እግዚአብሔርን ከማስደሰት የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ ከታየን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ማስተካከል አለብን፡፡ወይም ደግሞ ከሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜን እንዳታሳልፉ እና ከእግዚአብሔር ይልቅ የዛን ሰው ትኩረት እና ተቀባይነት ይበልጥ እንድትፈልጉ እያደረጋችሁ ይሆናል፡፡በመጨረሻም መሆን ያለበት በህይወታችን በመንፈስ ቅዱስ ከመመራት ወይም ለእግዚአብሔር ከመኖር የሚከለክለን  ማንኛውም ሁኔታም ሆነ ፍላጎት ጤናማ እና ለእኛ ጥሩ ያልሆነ ረብሻ ነው፡፡

እግዚአብሔር በመንፈሱ እንጂ በሚረበረሹን ነገሮች እንድንመራ አይፈልግም፡፡ስለዚህ ዛሬ የህይወትን ረብሻዎች ሁሉ ወደጎን አድርጋችሁ በአላማ በእግዚአብሔር ላይ አተኩሩ፡፡በመጀመሪያ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ ስትፈልጉ ታገኙታላችሁ፡፡ሁልጊዜም እናንተን እየጠበቀ አለ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ቢያምምም እንኳ በህይወቴ ያሉትን የሚረብሹ ነገሮች ሁሉ እንዳስወግድ እንድትረዳኝ እጠይቅሀለሁ፡፡ከሁሉም ነገር በላይ አንተን እንድፈልግህ እና በየዕለት ተዕለት ህይወቴ በመንፈስ ቅዱስ እንድመራ እርዳኝ፡፡ለአንተ መኖር እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon