የሚቻልህን አድርግ

ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣ – ፊሊጲሲዩስ 1፡10

ግዚአብሔር የላቀ ነው፡፡  እርሱን የምንወክል ሰዎችም የላቅን መሆን ይገባናል፡፡  እጃችንን የምናስገባበትን የትኛውም ነገር የሚቻለለን ሁሉ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡  እንሰራዋለን የምንለውን የትኛውንም ነገር በተነሳሽነት እና  የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ማከናወን ተገቢ ነው፡፡  ጳውሎስ  የሚሻላን እና ሽልማት የሚያስገኘ የላቅ እሴት  ለይተን ማወቅ እንዳለብን ይመክረናል፡፡ (ፊሊ 1፡10)  ልህቀትን የሕይወታችን መንገድ ስናደር  የእግዚአብሔር ደስታ በእኛ ከመሆኑም በላይ ለዓለምም የምንታይ  በጎ ምሳሌዎች እንሆናለን፡፡

የላቀ ነገር ለማጨድ የላቀ ነገር መዝራት አለብን፡፡  የልህቀትን ሕይወት ሳንኖር በሕይወታችን የላቁ ውጤቶችን መጠበቅ አይቻለንም፡፡  መጽሀፍ ቅዱስ  ትጋትን ፣ ቅልጥፍናን እና ቆራጥነትን በማዳበር የልህቀት ሕይወትን መኖር እንዳለብን ያስተምራል፡፡

እኔም በዚሁ አቅጣጫ እግዚአብሔር በመንገዳችሁ ላይ ያስቀመጠውን መርሃ ግብር ወይም የትኛውንም ስራ  በልህቀት እንድትሰሩ አበረታታኋለሁ፡፡ ሳትሰሩት የሚቀር ስራ አይኑር ፤ በምትችሉት አቅም ሁሉ በተሻለ አፈጻጸም አከናውኑት፡፡ አዕምሯችሁን በቅልጥፍናና በቁርጠኝነት አስታጥቁ፡፡ የላቁ ውጤቶችን ለማግኘት ራሳችሁን ስጡ፡፡  እግዚአብሔር የልህቀት አቋምን ያከብራል፡፡ የምትችሉትን ምርጡን ለማድረግ ምረጡ በዚያም እግዚአሔር በሂደት ውስጥ  ኃይልን ያስታጥቃችኋል፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ  የልህቀትን ሕይወት መኖር እፈልጋለሁ፡፡  በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኘየ የማከናውነውን የትኛውንም ስራ በታላቅ ቅልጥፍና ፣ ትጋት እና ቆራጥነት እንዳከናውን እርዳኝ ፤ አበረታኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon