የማይገባችሁን ማግኘት

የማይገባችሁን ማግኘት

እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ጩኸቴንም ሰማ፡፡ከሚውጥ ጉድጓድ፣ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤እግሮቼን በአለት ላይ አቆመ፤አካሄዴንም አጸና፡፡ – መዝ 40፡1-2

በጣም አብዛኛዎቹ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የሚፈቅዱት ይገባኛል ብለው ሲያምኑ ብቻ ነው፡፡አንድ ወቅት በህይወቴ ልክ እንደዛ ነበርሁ፡፡ለአመታት እግዚአብሔር ሊረዳኝ የሚገባው እንዲረዳኝ የሚያደርግ በቂ ጥሩ ነገር ሳደርግ ብቻ እንደሆነ ይሰማኝ  ነበር፡፡

እንደዚያ ያለ አስተሳሰብ የምስጋናን አመለካከከት አይፈጥርም፡፡የምንቀበለው የሚገባንን ብቻ ነው ብለን ካሰብን ስጦታ ሳይሆን ደሞዝ ወይም “ለተሰጠ አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ” ይሆናል፡፡ያልተገባንን በመቀበልና የተገባንን በመቀበል መሀከል ማለት በጸጋ እና በስራ መሀከል ያለው ልዩነት ነው፡፡

ልባችሁን ከፍታችሁ የእግዚአብሔር ጸጋ ወደ እናንተ እንዲመጣ እና በየዕለት ተዕለት እርምጃችሁ እንዲረዳችሁ እንድትፈቅዱለት አበረታታችኋለሁ፡፡ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲሰማችሁ በራሳችሁ ጥረት እየኖራችሁ ስለሆነ እንደሆነና በእናንተ እንዲሰራ በመፍቀድ ወደ እግዚአብሔር ጸጋ መመለስ እንዳለባችሁ አስታውሱ፡፡

እግዚአብሔር ውለታ እንዲውልላችሁ መፍቀድን ተማሩ፡፡የእግዚአብሔር እርዳታ የተገባችሁ ሰዎች ለመሆን መጣር አቁሙና የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እንዲያሟላላችሁ ፍቀዱለት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ የተገባኝ ሲመስለኝ ብቻ እርዳታህን መቀበልን መፍቀድ ሞኝነት መሆኑ ገብቶኛል፡፡የራሴን ስራዎች ትቼ ያንተን ጸጋ እቀበላለሁ፡፡በእያንዳንዱ ሁኔታ በማይገባኝ ጊዜም ውስጥ ስለምትረዳኝ አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon