የምታስቡትን አስቡ

የምታስቡትን አስቡ

በመቀጠልም፣ “ስለምትሰሙት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ይጨመርላችኋል። – ማርቆ 4፡24

አማኝ ከሆናችሁ ምናልባት በእያንዳንዱ ቀናችሁ የምታስቡትን ሃሳብ መፅሃፍ ቅዱሳዊ በሆነ ሃሳብ ልታስቡ ትችላላችሁ፡፡ ነገርግን ይህንን አስተውሉ በአዕምሯችሁ የሚመጣውን ማንኛውንም ሃሳብ ነው የምታስተናግዱት ወይስ ቀና የሆነውን ብቻ? በአዕምሮዬ የሚመላለሰው ነገር አንድም ሰይጣን ያቀረበልኝ የውሸት ሃሳብ አሊያም ባዶ የሆነ ባተሌ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፡፡

ማርቆሰ 4፡24 አንብቡ ይህ ክፍል የሚናገረው በየጊዜው ሊያራምደንና በኃይል ሊሞላን ስለሚችል ማሰብ ስለሚገባን ነገር ነው፡፡የክፍሉ ሃሳብ ቃሉን በሚገባው መጠን ማንበብና ማድመጥ ስንጀምር ብዙ መረዳትና መገለጦችን እያገኘን እንሄዳለን፡፡

በስጋችን ደካሞች ስለሆንን ምንም ሳንደክም ከእግዚያብሔር ለመቀበል የተለያዬ ጥረቶችን እናደርጋለን ይሁን እንደዚህ አይሰራም፡፡ ከቃሉ መውሰድ የምትችሉት በምታወጡት ጥረት ልክ ነው። የእግዚያብሔርን ቃል ዕለት ተዕለት እንድታንሰላስሉትና እንድታነቡት አበረታታችኋለሁ ሁል ጊዜም ይህንን ማድረጋችሁን ከቀጠላችሁ እውቀትና በረከትን ትቀበላላችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ቃልህን ዕለት ተዕለት ለማንበብና ለማንሰላሰል ቃል እግባለሁ፤ ይህንንም በማደርግበት ጊዜ ብዙ እውቀትና በረከትን ከአንተ እንደምቀበል አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon