የምድረበዳን አስተሳሰብ ማሸነፍ

የምድረበዳን አስተሳሰብ ማሸነፍ

እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ አለን፤እነሆ በዚህ ተራራ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል፡፡ – ዘዳ 1፡6

እስራኤላዊያን በምድረበዳ የአስራአንድ ቀን መንገድ ለመጨረስ ለአርባ አመት ተንከራትተዋል፡፡ለምን?

አንዴ እዚህ ጉዳይ ላይ በጣም ሳስብ ጌታ እንዲህ አለኝ፣”እስራኤላዊያን ወደፊት መሄድ ያቃታቸው የምድረበዳ አስተሳሰብ ስለነበራቸው ነው፡፡”እስራኤላዊያን ለህይወታቸው ምንም አይነት አዎንታዊ ራዕይም ሆነ ህልም አልነበራቸውም፡፡ይሄንን አስተሳሰባቸውን ጥለው እግዚአብሔርን ማመን ነበረባቸው፡፡

እስራኤላዊያንን በመገረም ማየት የለብንም ምክንያቱም ብዙዎቻችን እነርሱ ያደረጉትን ተመሳሳይ ነገር እያደረግን ነው፡፡ ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ተመሳሳይ ተራራ እየዞርን ስለሆነ በአጭር ጊዜ ማለቅ በሚችል አንድ ነገር ላይ ድልን ለማግኘት አመታት ይፈጅብናል፡፡

አዲስ አስተሳሰብ ያስፈልገናል፡፡የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን ማመን መጀመር አለብን፡፡ማቴ.19፡26 ሲናገር ከእግዚአብሔር ጋር ሁሉም ይቻላል፡፡የሚፈልገው በእርሱ ላይ ያለንን እምነት ብቻ ነው ሌላውን የሚሰራው እርሱ ነው፡፡

እግዚአብሔር ዛሬ ለእኔና ለእናንተ የሚለን ነገር ለእስራኤል ልጆች ካላቸው ነገር ጋር ተመሳሳይ ነው፡እነሆ በዚህ ተራራ ለረጅም ጊዜ ቆይታችኋል…ጉዞ ቀጥሉ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በህይወቴ ተመሳሳይ አሮጌ ተራራዎችን በመዞር በቂ ጊዜ አሳልፌያለሁ፡፡ከአንተ ጋር ወደፊት መሄድ እንደምችል አውቃለሁ ስለዚህ እምነቴን በአንተ ላይ አድርጌ የምድረበዳን አስተሳሰብ እተዋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon