
እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአንደበቱም እዉቀትና ማስተዋል ይወጣል፡፡ – ምሳሌ 2:6
ህይወት ደስ አይልም ስሜቶቻችን እንዲመሩን ስንፈቅድ ፡፡ ስሜቶች ከቀን ወደ ቀን፣ ከሰዓት ወደ ሰዓት ከቅጽበት ወደ ቅጽበት የሚቀያየሩ ናቸዉ፡፡ አብዛኛን ጊዜ ይዋሹናል፡፡ በአጭሩ ስሜቶቻችንን ልናምናቸዉ አንችልም፡፡
ነገር ግን እኛ መምረጥ እንችላለን፤ ልክ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች የሐሰት ስሜቱን ችላ ብለን በእዉነትና በጥበብ መኖር ማለት ነዉ፡፡ እስኪ ጥቂት ምሳሌ ልስጣችሁ፦
ምንአልባት ራስህን በህዝብ በተጨናነቀ ቦታ አግኝተሀዋል እንበል ከዚያም ሰዉ ሁሉ ስለ አንተ እያወራ እንደሆነ ተሰምቶሃል፤ ያ ማለት እነርሱ እያወሩ ነዉ ማለት አይደለም፡፡ ሰዎች በትክክል እንደማይረዱህ፣ እንደማያደንቁህና እንደሚበድሉህ ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንተ እንደዚያ ነህ ማለት አይደለህም፤ እነዚህ ስሜቶች ብቻ ናቸዉ፡፡
በሳሎች፣ በምግባር የታነጽንና በመንፈሱ ለመሄድ የወሰንን ሰዎች መሆን ያስፈልገናል፡፡ ከራሳችን መንገድ ይልቅ በእግዚአብሔር መንገድ ነገሮችን ለማድረግ ቀጣይነት ያለዉ የፈቃደኛነትን መምረጥ ይጠይቃል፡፡
አንዳንድ ጊዜ በቦንብ የተደበደብን ያህል በአሉታዊ ስሜቶች ልንጠቃ እንችል ይሆናል፤ እነዚያ ስሜቶች እንዲቆጣጡሩንና ሕይወታችንን እንዲበክሉ ልንፈቅድላቸዉ አይገባም፡፡ በምትኩ እዉነትን፣ እግዚአብሔራዊ ጥበብንና ዕዉቀትን መከተል እንችላለን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ! ስሜቶቼ ዘወትር ከአንተ ጥበብ በተቃራና ለመጓዝና ሊጉዶኝ ይሞክራሉ ግና ሕይወቴን እንድመሩት አልፈቅድላቸዉም፡፡ ዘወትር በሚለዋወጡ ስሜቶቼ እንዳልያዝና ከአንተ ጋር እንድጣበቅ ወደ እዉነትህ ምራኝ፡፡