የሰው ተፈጥሮ መረዳት

የሰው ተፈጥሮ መረዳት

ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር ፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመንባቸውም ነበር ፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና፡፡ – ዮሀንስ 2፡24-25

በአንድ ወቅት በሚያሳዝን የቤተክርስቲያን ብስጭት ውስጥ ነበርኩኝ ፤ እግዚአብሔር ዮሀ 2፡24-25 ያለውን ክፍል እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ ክፍሉ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ስለነበርው ግንኙነት ያወራል፡፡ በግልጽ ቋንቋ ኢየሱስ ራሱ አይተማመንባቸው ነበር ይላል፡፡ ራሱን አብረውት ለነበሩ ሰዎች ቢሰጥም ግን እነሱ ፍጹም እንዳልሆኑ ግን ያውቅ ነበር፡፡ የሰውን ተፈጥሮ ተረድቷል፡፡ ባልተመጣጠነ መንገድ አይተማመንባቸውም ነበር ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ መተማመን ሲገባኝ በሰዎች ላይ መተማመን ወደ ብስጭት መንገድን ወስዶኛል፡፡

በየትኛውም ግኑኝነታችን ብዙ ርቀት ልንጓዝ እንችላለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጥበብ ውጭ ብንሄድ በእርግጥም እንጎዳለን፡፡ ሰዎች መቼም አይጎዱንም በሚል ወጥመድ ውስጥ ልንወድቅ እንችላለን እናም ሰዎች በሰጠናቸው ደረጃ የማይገኙ እንደሆነ በሰተመጨረሻ ልንበሳጭ እንችላለን፡፡ ማንም ፍጹም አይደለም፡፡

መልካሙ ዜና እግዚአብሔር ፍጹም ነው ፤ ማንንም አያበሳጭም፡፡ እርሱ ዘወትር ፍቅር እና መልካም ነው፡፡ መታመን እግዚአብሔር እያለ መታመንን በሰዎች ላይ አታድርግ ባይሆን ለእርሱ ሙሉ በመሉ ራስህን ስጥ፡፡ እርሱ ብቻውን ሙሉ በመሉ ታማኝ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ማንም ሰው ፍጹም አይደለም ፤ አንተ ግን ፍጹም ነህ፡፡ ሁል ጊዜ በአንተ ለመታመንና እንደማታበሰጨም በአንተ መደገፍ እሻለሁ፡፡ በአንተ ፍጽምና ውስጥ ዛሬ መጽናናት አግቻለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon