የቃል ኪዳን ምድርህን ለመዉረስ ቁልፉ

ተስፋ የምታደርገዉ ለምንድነዉ?

እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስሮች ሆይ፥ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ ሁለት እጥፍ አድርጌ እንድመልስልሽ ዛሬ እነግርሻለሁ። – ት.ዘካ 9:12

እኔ ለአንተ ጥያቄ አለኝ፡ ተስፋ እያደረግህ ያለሀዉ ለምንድነዉ? በሕይወትህ የምትጠብቀዉ ምንድነዉ? አንድ አዲስና መልካም ነገር እንደሚከሰት ተስፋ እያደረግህ ነዉ ወይስ ተስፋ ቆርጠሃል?

ዛሬ ዛሬ ብዙ ሰዎች ተስፋ-ቢስነት ይሰማቸዋል፡፡ ለማንኛዉም ኢየሱስ የሞተዉ ተስፋ-ቢስ እንድንሆን አይደለም፡፡ እርሱ የሞተዉ እኛ በተስፋ እንድንሞላ ነዉ፡፡

ዲያብሎስ ተስፋህን መስረቅ ስለሚፈልግ ይዋሽሃል፡፡ በህይወትህ ምንም መልካም ነገር እንደማይገጥምህና አሁንም ያሉህ መልካም ነገሮች እንደማይዘልቁ ይነግርሃል፡፡ በከባድ ሁኔታ ዉስጥ እየታገልህ ከሆንክ ይህ ችግር እንደማይቆም ይነግርሃል ነገር ግን በተስፋ ተሞላ ዲያብሎስ ሀሰተኛ እንደሆነም አስብ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር መቀየር ይችላል፡፡

አባታችን መልካም ነዉ፤ ደግሞም ለህይወትህ ያለዉ ዕቅድ መልካም ነዉ፡፡ በተስፋህ ከቆየህ በተለይም ደግሞ በመከራና ባለመረጋጋት መሃል ከጸናህ ለተቸገርከው እጥፍ እንደሚሰጥህ ቃል ይገባልሃል ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ነገር፣ አንድ መልካም ነገር እንዲያደርግ ጠብቅ!


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ተስፋዬ በአንተ ነዉ፡፡ ሳይጣን ዉሸታም ነዉና አልሰማዉምተስፋም አልቆርጥም፡፡ በህይወቴ መልካም ነገር እንደምታደርግ እጠብቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon