የቆመችን መኪና ለመንዳት አትችልም

የቆመችን መኪና ለመንዳት አትችልም

«አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ» (መዝ.119፡133)።

ብዙ ሰዎች ብዙ ጊዜ «እግዚአብሔር በህይወቴ እንዳደርግ የሚፈልገውን ነገር እንዴት ማወቅ እችላላሁ?» ብለው ይጠይቃሉ። አንዳንድ ሰዎች ከሰማይ ማድረግ የሚገባቸውን ድምጽ እስከሚሰሙ ድረስ በፍጹም ምንም ሳይንቀሳቀሱ በአንድ ሥፍራ ረጅም ጊዜ ያሳልፋሉ።

በእንደዚህ ዓይነት አቋም ላይ ላሉ ሰዎች የእኔ ምክር በቀላሉ አንድ ነገር እንዲያደርጉ ነው። እግዚአብሔር አንድ ነገር እንድታደርግ እንደሚጠራህ ታስባለህና ያንን የታዘዝከውን ስታደርግ ከተሳሳትህ እርሱ እንድታስተካክለው ይረዳሃል። እግዚአብሔር ተናግሮኛል ብለህ ያመንከውን ነገር እሳሳታለሁ ብለህ በመፍራት ካለመታዘዝ ህይወትህን አታባክነው። እኔ አንዲህ ማለትን እወዳለሁ፣ «የቆመን መኪና መንዳት አትችልም» እግዚአብሔር እንድትሄድበት የሚገባውን መንገድ እንዲያሳይህ ከፈለግህ የሚያስፈልግህ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው። ካልተንቀሳቀስህ በስተቀር እርሱ «ወደ ቀኝ ታጠፍ» ብሎ አንድ ነገር ሊናገርህ አይፈልግም። ነገር ግን አንተ ከተንቀሳቀስህ፣ እርሱ አቅጣጫ ይሰጥሃል።

በዚህ ሥፍራ አንድ የጥበብ ቃል ልጠቀም። አንዳንድ ጊዜ መረጋጋት የሚያስፈልገን ጊዜ አለ፣ በጸሎት እርሱ ፊት እንድንቆይና ወዲያውኑ አርምጃ የማንወስድበት የተወሰኑ ጊዜያቶች አሉ። ነገር ግን ይህ በሁሉም ሁኔታዎቻችን ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ማለት ማለት አይደለም። ለተወሰኑ ጉዳዮች የእርሱን ምሪት ተቀብለን ለመንቀሳቀስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈለግ የምንችልባቸው አንዳንድ ጊዜያት አሉ፣ እርሱም ደግሞ ልንቀሳቀስበት እንድንችል ይናገረናል፣ ይመራናልም። ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ስንጘዝም እንኳን የምንሄድበትን መንገድ ይዘጋውና ሌላ አዲስ በር ይከፍትልናል።

ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ ጸሎትን ስትጸልይ ከእርሱ ጋር በትክክል በመስማማት በመጓዝ ላይ እንዳለህ እርግጠኛ ሁን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon