የበለጠ መስማት ትፈልጋለህ?

የበለጠ መስማት ትፈልጋለህ?

አምላካችሁን እግዚአብሔርን ተከተሉ [በአክብሮት] ደግሞም እርሱን ፍሩ፣ ትእዛዛቱንም ጠብቁ፣ ድምፁንም ታዘዙ፣ እርሱን አገልግሉት ደግሞም ከእርሱ ጋር ተጣበቁ። (ዘዳግም 13: 4)

ከእግዚአብሔር ለመስማት የምንጠብቅ ከሆነ ድምጹን መስማት አለብን። ሁል ጊዜ ከእርሱ ለመስማት ከፈለግን ለመታዘዝም ፈጣን መሆን አለብን። በልባችን ውስጥ ድምጹን ለመስማት ያለን ዝንባሌ በመታዘዝ ጨምር ደግሞም ባለመታዘዝ ሊቀንስ ይችላል። አለመታዘዝ የበለጠ አለመታዘዝን ይወልዳል፣ መታዘዝ ደግሞ ወደ በለጠ ታዛዥነት ይመራል።

ከእንቅልፋችን እንደነቃን “ስጋዊያን” ሆነን እንደምንውል የምናውቅባቸው አንዳንድ ቀናት አሉ። ቀኑን ግትር እና ሰነፍ፣ ብስጩ እና ነገረኛ ሆነን እንጀምራለን። የመጀመሪያ ሀሳቦቻችን፦ ዛሬ ሁሉም ሰው ብቻዬን እንዲተወኝ እፈልጋለሁ፤ ይህንን ቤት አላጸዳም፥ ወደ ገበያ እሄዳለሁ፤ ክብደት የመቀነስ ዕቅዴን እተወዋለሁ፣ ቀኑን ሙሉ መብላት የምፈልገውን እበላለሁ። እናም ማንም ስለዚህ ጉዳይ ምንም ነገር እንዲለኝ አልፈልግም።

እንደነዚህ ባሉ ቀናት የምናደርገው ውሳኔ አለ። እነዚያን ስሜቶች መከተል እንችላለን ወይም “አምላኬ እባክህ እርዳኝ፣ በፍጥነት አድርገው!” ብለን መጸለይ እንችላለን።አመለካከቶቻችንን እንድናስተካክል እንዲረዳን በቀላሉ ከጠየቅነው ስሜቶቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ስር ሊሆኑ ይችላሉ። ስጋዊያን ስለሆኑ ቀናት ሁሉንም አውቃለሁ፣ በመጥፎ ልንጀምር እንደምንችል ከዚያም የባሰ ልንሆን እንደምንችል አውቃለሁ። ለራስ ወዳድነት አመለካከት ከተሰጠንና ሥጋችንን ከተከተልን በኋላ ቀኑን ሙሉ እንዲሁ እንውላለን። ነገር ግን ህሊናችንን በታዘዝን ቁጥር እግዚአብሔር በመንፈሱ ሊመራን የሚችልበትን መስኮት እንከፍታለን። የእግዚአብሔርን ድምፅ በምንታዘዝበት ጊዜ ሁሉ ለሚቀጥለው ጊዜ የበለጠ ብርሃንን ያስገባልናል። እግዚአብሔርን የመከተል ደስታ አንዴ ካወቅን ያለእርሱ ለመኖር ፈቃደኞች አንሆንም።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ዛሬ ስጋዊ የሆነ ቅን እንዲኖርህ አትፍቀድ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon