የበረከት ህይወት መኖር

የበረከት ህይወት መኖር

ስለዚህ እድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካም እናድርግ፡፡ – ገላቲያ 6፡10

ንደ ክርስቲያን ካሉን ትልልቅ ዕድሎች አንዱ በሌሎች ህይወት ውስጥ መሰረታዊ ልዩነት ማምጣት መቻላችን ነው ብዬ አምናለሁ፡፡በአገልግሎት ዘመኔ ሁሉ እግዚአብሔር ምሪትን ለሚፈልጉ ብዙ ሰዎች ከቃሉ ትምህርትን የማካፍልበት ዕድል ሰጥቶኛል፡፡

ነገር ግን ይሄ እግዚአብሔር ለእኔ ብቻ የሰጠው ልዩ ዕድል ነው ብዬ አላምንም፡፡ሁሉም ሰው እናንተን ጨምሮ ሰው ላይ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም አለው፡፡ሌላን ሰው ለመድረስ ጊዜ ስትወስዱ እና በአንድ ሰው ህይወት ላይ ዋጋን ስትከፍሉ በራሳችሁ እና በሌላው ሰው አለም ላይ ተጽዕኖ እየፈጠራችሁ ነው፡፡

ገላቲያ 6፡10 እግዚአብሔር በመንገዳችን ለሚያመጣቸው ሰዎች ሁሉ መልካምን እንድናደርግ ይነግረናል፡፡የተጠራነው በረከት ለመሆንና ሌሎችን በእምነት ለመገንባት ነው እንጂ ሰዎችን መድረስና እውነትን በፍቅር መናገር የምንፈራ እንድንሆን አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በህይወታችን ከተመልካች በላይ እንድንሆን እንደሚፈልግ አምናለሁ፡፡ሌሎችን የምንወድ እና በህይወታቸው ላይ ዋጋን ለመክፈል ግድ የሚለን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡እንዲያድጉ እና ሌሎች ብዙ ሰዎችን እንዲደርሱ ሌሎችን በኢየሱስ ስም ማነጽ አለብን፡፡

ብታውቁትም ባታውቁትም እናንተን የሚያይእና ከእናንተ የሚጠብቅ አንድ ሰው አለ፡፡ሰዎች እናንተ በምትኖሩበት መንገድ ተጽዕኖ ስር ስለሚወድቁ በዕለት ተዕለት ድርጊቶቻችሁ የእግዚአብሔርን ፍቅር ማየት አለባቸው፡፡

አንዳንዴ ስህተት እንሰራለን እናም ይሄኔ ጌታን ስለ ምህረቱ ማመስገን ይኖርብናል፡፡ነገር ግን ለአንዳንድ ሰዎች ምናልባት የሚያዩት ብቸኛ የእግዚአብሔር ማስረጃዎች እናንተ እንደሆናችሁ ማወቅ አለባችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በእያንዳንዱ ቀን አንድን ሌላ ሰው ደግሞ በፍቅርህ የምደርስበት፣የምባርክበት እና ተጽዕኖ የማመጣበት የሰጠኸኝ ሌላ መልካም አጋጣሚ አለ፡፡እግዚአብሔር ላይ ያተኮረ ህይወት መኖር ምን ማለት እንደሆነ በማሳየት ሌሎችን የሚባርክ ህይወት መኖር እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon