የተስፋ መልህቅ

የተስፋ መልህቅ

እኛም የነፍስ መልህቅ የሆነ ጽኑና አስተማማኝ ተስፋ አለን፤ይህም ተስፋ ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ውስጠኛ መቅደስ ይገባል፡፡ – ዕብራ 6፡19

ሁላችን በህይወታችን ውስጥ ከባድ ጊዜዎችን እናሳልፋለን እናም በማዕበል ውስጥ እንዳለ መርከብ ተረጋግቶ ለመቆም ዕርዳታ ያስፈልገናል፡፡ መርከብ እንዲረጋጋ የሚረዳው መልህቅ አለው መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር ደግሞ የእኛ መልህቅ ተስፋ ነው ይላል፡፡

እኔ እና እናንተ ተስፋችንን በእግዚአብሔር እና በቃሉ ላይ ስናጸና ንፋሱና ማዕበሉ ሊሰማን ይችላል ነገር ግን በመጨረሻ አንናወጥም፡፡

በማዕበል ጊዜ ፤ ተስፋ ነገሮችን እንዳሉ የምናይበትን ችሎታ እና የተሻለ ነገር እየመጣ እንደዳለ መተማመንን ይሰጠናል፡፡ ይሄም ተስፋን ለእኔና እናንተ እንዲኖረን የሚገባ በጣም ሀይለኛ እና አስፈላጊ ብቃት ያደርገዋል-በተለይ በችግር ወቅት፡፡ እውነት ለመናገር እምነታችን ሊገነባበት የሚገባ መሰረት ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡

ችግር ወይም ሀዘን በፍጹም ሊያጋጥመን እንደማይችል ማንም-እግዚአብሔርም ቢሆን-ቃል ሊገባልን አይችልም፡፡ ነገር ግን አስፈላጊው ነገር ተስፋ ማድረግ አለማቆማችን ነው፡፡ አዎንታዊ አመለካከት ሲኖረንና በክርስቶስ ያለንን ተስፋ ስንይዝ የክርስቶስን ተአምር ሰሪ ሀይል የምናይበት ቦታ ላይ እንቀመጣለን፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ተስፋዬን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡ በከባድ ጊዜ በአንተ ላይ ያለኝ እምነት እና በህይወቴ ታላላቅን ነገሮች እንደምትሰራ ያለኝ መጠባበቅ መልህቄ ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon