የኢየሱስ ደም

የኢየሱስ ደም

እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። – 1 ኛቆሮ 15:45

ኢየሱስ ደም መሰረተ ሀሳብ አንዳንድ ሰዎችን ያደናግራል ግና አማኞችም ቢሆኑ በትክክል ካልተረዱት በስተቀር የደሙን ሀይል አይጠቀሙም፡፡

አዳም ኀጢአት ሲሰራ ኀጢአቱ ወደ ሁሉም የተላለፈዉ በደሙ በኩል ነበር፡፡ ይህንን እዉነት ዳዊት በመዝሙር 51፡5 ላይ “እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።” ሲል አረጋግጧል፡፡

ኢየሱስ የመጣዉ የሰዉል ዘር ሊዋጅ፣ ነጻነታችንን ሊገዛና ወደ ቀደመዉ ቦታችን ሊመልሰን ነዉ፡፡ ታዲያ ይህንን እነዴት በኀጢአተኛ ደም ሊያደርግ ይችላል?

በ1ኛ ቆሮ 14፡45 ላይ ኢየሱስ የኋለኛዉ አዳም ተብሎ ነዉ የተነገረን ምክንያቱም እርሱ የተወለደዉ ከሰዉ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነዉ፡፡ በኢየሱስ ደም ዉስጥ ህይወት አለ ይህ በአግባቡ ሲተገበር በደሙ ዉስጥ ያለዉ ህይወት በእኛ ዉስጥ በኀጢአት ምክንያት ይሰራ የነበረዉን ሞት ገጥሞ ድል ነስቶታል ማለት ነዉ፡፡

እግዚአብሔር የኛ ወደሆነዉ የሥልጣን ቦታ ሊመልሰን ይፈልጋል፡፡ ሁሉንም ቅንብር ቀድሞዉኑ ሰርቶት ነበር ይህንን “ፊርማዉን አኑሮአል” ማለት እንችላለን፡፡ የግዢዉ ዋጋ በሙሉ ተከፍሎአል፡፡ እኛ በዉዱ የኢየሱስ ደም ተገዝተናል፡፡


የጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በኢየሱስ ደም ተዋጅቼአለሁ ነጻም ወጥቼአለሁ፡፡ የተወለድኩት በኀጢአት ቢሆንም የኢየሱስ ደም አንጽቶኛል፡፡ ጌታ ሆይ አመሰግንሃለሁ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon