የእውነተኛ ክርስቲያን ምልክት

የእውነተኛ ክርስቲያን ምልክት

እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፡፡ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋር አብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኩራሩ፣በራሳችሁም አትመኩ፡፡ – ሮሜ 12፡16

አንዱ በጣም አስፈላጊ የፍቅር መገለጫ ራስ ወዳድ አለመሆን ሲሆን በሮሜ 12፡16 ላይ በፍቃደኝነት ዝቅተኛ ኑሮ ላይ ካሉ ጋር አብሮ መኖርን ይገልጸዋል፡፡

የዚህ ቃል ትርጉም የገባቸው እና በህይወታቸው የተጠቀሙበት ሰዎች በፍቅር ራሳቸውን ዝቅ ማለትን ያውቁበታል፡፡ራስ ወዳድ አይደሉም፡፡ከሌሎች ጋር ተስማምቶ እና ተላምዶ መኖርን ተምረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ማሰብ ካለባቸው በላይ ስለ ራሳቸው ከፍተኛ አመለካከት ያላቸው ሰዎችደግሞ ከሰዎች ጋር ተላምዶ መኖር ይከብዳቸዋል፡፡ስለራሳቸው ያላቸው ከፍ ያለ አስተሳሰብ ሌሎችን እንደ “ትንሽ” እና እንደ “የማይጠቅሙ” አድርገው እንዲያዩ ያደርጋቸዋል፡፡ከራስ ወዳድነታቸው የተነሳ ሌሎች ከእነርሱ ጋር እንዲስማሙ እንጂ እነርሱ ግን ሌሎችን ሳይናደዱ እና ሳይበሳጩ ማስተናገድ አይችሉም፡፡

እናንተ የትኛው አይነት ሰው ናችሁ? እኔ በጣም ራስ ወዳድ ሰው ነበርሁ፣አሁን ግን ከልምድ ራስ ወዳድ ሳይሆኑ የበለጠ አርኪ የመኖር መንገድ እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡

የእውነተኛ ክርስቲያን ምልክቱ ከሌሎች ጋር የመስማማት ችሎታው ነው፡፡ዛሬ ከሌላ ሰው ጋር ከራስ ወዳድነት በጸዳ መልኩ መስማማት ትችላላችሁ?


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በየዕለቱ ከሌሎች ጋር በፍቅር እንዴት መስማማት እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡በቻልኩ ጊዜ ሁሉ ራስ ወዳድ ባለመሆን የሌሎችን ፍላጎት በማሳካት ለመስማማት እፈልጋለሁ፡፡በፍቅርህ ልቀርባቸው እንደሚገባ አሳየኝ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon