
የእውነትን ቃል በቅንነት የሚያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ 2ኛጢሞ 2÷15
ማንም የእግዚአብሔርን ደምፅ መስማት የሚፈልግ ሰው የቃሉ ተማሪ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ልነገረን ከሚመርጣቸው ብዙ መንገዶች ሁሉ ከተፃፈው ቃሉ ጋር የሚጋጭ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ቅጂ በግሪክ ‹‹ለጎስ›› የተባለውን የሚቃረን አይደለም፡፡ የጊዜው (የንግግር) ቃል በግሪክ ቋንቋ ‹‹ሬማ›› ይባላል፡፡ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ጉዳያችን ወደ ትውስታችን ቃሉን (ሎጎስ) ወደ ጉዳያችን ያመጣል፡፡ የእርሱ ‹‹ሬማ›› የጊዜው ቃል (እግዚአብሔር በድምፅ ለእኛ የሚናገር) ምናልባት ቃል በቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ገጽ ላይ ላይገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን አግባብነቱ ሁልጊዜ በተፃፈው ቃል ይደገፋል፡፡ በዚህ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ የሰማነው ድምፅ ከእግዚአብሔር መሆኑን አለመሆኑን ያረጋግጣል፡፡ ለምሳሌ፡- ሎጎስ፡- የተፃፈው ቃል አዲስ መኪና መች እንደምንገዛና መች እንደምንገዛ አይነግረንም፡፡ ለዚያ የጊዜው ቃል (የእግዚአብሔር ድምፅ) ወይም ‹‹ሬማ›› ቃል ያስፈልገናል፡፡ ምንም እንኳ ቃሉ ውስብስብ የሆኑ መመሪያዎችን መኪናውን በመግዛት ጉዳይ ባይሰጠንም እንኳ ስለእግዚአብሔር ጥበብ ብዙ የሚል ነገር አለው፡፡ በጣም ውድ የሆነ አዲስ መኪና ለብዙ ዕዳ የሚዳርግና ለአመታት በብድር ስር የሚካተት ከሆነ በቀላሉ መኪናውን የገዛንበት መንገድ ጥበብን በተሞላ አይደለም፡፡ እንዲሁም የሰማነው ድምፅ ራሱ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ሎጎስ ተ ሬማ =ጥበብ