‹‹ … እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ›› (ዕብ.6፡15) ።
እግዚአብሔር ለአብርሃም ለዘሩ የውርስ የተስፋ ቃል ሰጠው፤ ነገር ግን ሊገምተው ከሚችለው በላይ ይህንንየተስፋ ቃል ይጠብቀው ነበር፡፡ የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ‹‹አብርሃም ለብዙ ጊዜ ጠበቀ፤ በትዕግስትም ጽና›› ብሎ ይናገራል፡፡ በእነዚ ጊዜያት እርግጠኛ ነኝ እውነተኛውን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ደጋግሞ ደጋግሞ እያስታወሰ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜያት የተራዘመው የተስፋ ቃል ስንጠብቅ /ከመጠበቃችን የተነሳ/ ከእግዚአብሔር የምንሰማውን ማንኛውንም ነገር ከመስማት ወደ መጠራጠር እናዘነብላለን፡፡ ምናልባት አንተም በአሁኑ ሰዓት አንድ ነገር እየጠበቀህ ይሆናልና፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ለልብህ የተናገረህን የተስፋ ቃል ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡
አብርሃም የምስጋናና የውዳሴ መስዋዕት በሰዋ ዕለት ጥርጣሬና አለማመን ያጠቃው ነበር፡፡ ሰይጣን እኛን በሚዋጋንበት ጊዜ ምንም እርምጃ ከመውሰድ ዳተኛ መሆን የለብም፡፡ የእርሱን ወሸት በእግዚአብሔር ቃልና የተስፋ ቃል በማስታወስ በእርሱ ላይ ጦርነት /ውጊያ/ መክፈት ይጠበቅብናል፡፡ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ከፍ ባለ ድምጽ መናገር ማሰላሰልና እነርሱን በማስታወሻ ላይ መጻፍ አለብን፡፡ እንባቆም እግዚአብሔርን በሚጠብቅበት ጊዜ እርሱ የተሰጠውን የተስፋ ል በዚያ በኩል የሚያልፈው ሁሉ ያነብበው ዘንድ ራዕዩን በገበታ ላይ /በወረቀት ላይ/ ይጻፍ ዘንድ አዘዘው (እንባ.2፡2)፡፡ ምናልባትም ይህ የብሉ ኪዳን ዘመን የማስታወቂያ ሰሌዳ ሊሆን ይችላል፡፡
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ እምነትህን አትብቀህ ያዝ፡፡ ምንም ዓይነት ስሜት ቢሰማህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ተስፋ አትቁረጥ ለአብርሃም በተቀጠረው ጊዜ የገባለትን የተስፋ ቃል እንደፈጸመለት ለአንተም ቃሉን ይፈጽማል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ሰለሚሰማህ ስሜት አትናገረው ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን ተናገረው፡፡