የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ፈልግ

በሁሉ አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና፡፡ የተሰ 5 18

ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት የሚፈልጉት አንዱና ዋናው ምክንያት በሕይወታቸው የእርሱን ፈቃድ እንዲነገራቸው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጂ ዓለማዊ ነገር በጣም ውስብስብ በማድረግና በማሰብ እንዲህ ይላሉ፡፡ እሺ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ካረጋገጥኩ፣ እታዘዛለሁ ወይም እኔ በእርግጥ እግዚአብሔርን መከተል እፈልጋለሁ፡፡ የእርሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡

እኔ አሁን የምነግርህ ስራ ስለመቀየርህ ወይም ወደ ሚንያ ፖሊስ ከተማ ስለመብረርህ ወይም ስለሚመጣው ፋሲካ በመጀመሪያ ረድፍ ላይ ትመጣለህ የሚል መለኮታዊ መልዕክት ሳይሆን አንድ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ የሆነ በሕይወትህ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ማወቅና መታዘዝ የምትችልበትን መንገድ አሳይዛለሁ፡፡ አመስጋኝ ሁን በምንም ውስጥ ብታልፍ ችግር የለውም ያ ትክክል ነው፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የልብ ጽናት ይኑርህ ያ ደግሞ ግልጽ የሆነ መንገድ ለሌሎ ነገሮች ሁሉ ይከፍትልሃል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምሥጋና በቀላሉ ይመጣና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ማመስገን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሕይወትህ የአመስጋኝነትን ባሕሪ ብታደርገውና ብታድሰው በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ትሆናለህ፡፡ አስተውል ከላይ ያለው ጥቅስ ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ እንድትሆን አያስገድድህም፡፡ በሕይወታችን በማንኛውም ነገር አመስጋኞች ለመሆን ከፈለግን የምናደርገውን ይነግረናል፡፡

ለምሣሌ፡- እንበልና አንድ ቀን ፍርጅ ከፍተህ ሰክተህ ማብራት ስለጠፋ ምግብህ በደንብ ስላልቀዘቀዘ መሆን እንዳለበት አልሆነም፡፡ ፍርጅ ኖሮህ ምግብህን የምታስቀምጥበት ስለሚኖርህ ልታመሰግን ትችላለህ፡፡ ያ አመስጋኝነትህ ፍርጁን በማደስ እንደገና ስሚኖርህ ልታመሰግን ትችላለህ፡፡ ያ አመስጋኝነትህ ፍርጁን በማደስ እንደገና እስክትጠቀምበት ድረስ በምስጋና መሆን ማለት ነው፡፡ በምታልፍበት ነገር ሁሉ ከቀን ወደቀን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በሕይወትህ ማመስገንን እንድትለማመዱ አበረታታሃለሁ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በሁሉ ነገር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon