የእግዚአብሔር ወዳጅ

የእግዚአብሔር ወዳጅ

ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወዳጆች ግን ብያችኃለሁ ዮሐ 15፡ 15

በዘፍ 18÷17 እግዚአብሔር አብርሃምን ወዳጄ ብሎ በመጥራት ሰዶምንና ገሞራን የማጥፋት እቅድ እንዳለው የልቡን ሃሣብ ገለፀላት፡፡ ልክ ለአብርሃም የልቡን ሃሣብ እንዳካፍለው እንዲሁ ከአንተ ጋር እንዲሁ ስለ ነገሮች ያካፍልሃል፡፡ ስለ ልቡ ሃሳብ፣ ስለ ፍላጎቱ፣ ስለ ዓላማው፣ እንደ ወዳጁ መረዳትህን ያስፋልህና የልቦና ዓይኖችህን ከፍቶልህ በሕይወትህ ምን ልሆን እንዳለ ይገልጽልህና ምን ማድረግ እንዳለብህ ይነግርሃል፡፡ ለወደፊቱ ይመራህና እንድትዘጋጅ ይረዳሃል፡፡ እንደ እግዚአብሔር ወዳጅ በሁኔታዎችህ ልትከበብ ወይም ለብቻ ልትጋፈጥ አይገባህም፡፡ ቀድሜህ መረጃ ልታገኝና ልትዘጋጅ ይገባሃል፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጅና ድምፁን የምትሰማ ሰው ነህ፡፡ ስለ እያንዳንዱ ጉዳይ አንተ ልታውቀው የምትፈልገውን ሁሉ ላይነግርህ ይችላል፡፡ ነገር ግን እርሱ ይመራሃል፣ ደግሞ በትዕግስት በታመንከው መጠን ብርታትህን ይሰጥሃል፡፡

ምናልባት ‹‹እንዴት የእግዚአብሔር ወዳጅ መሆን እችላለሁ; ብለህ ትጠይቅ ይሆናል፡፡ በዛሬው ጥቅስ መሠረት አንተ ቀድሞም የእግዚአብሔር ወዳጅ ነህ፡፡ በዚህ ጥቅስ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ‹‹እኔ ወዳጆቼ ብያቹሃለሁ›› አንተ የኢየሱስ ተከታይ ከሆንክ፡፡ አንተ የዘመኑ ደቀመዝሙርና የእርሱ ወዳጅ ነህ፡፡ እንደማንኛውም ወዳጅ ነህ ሁሉ ዝም ብሎ ትውውቅ፣ ወይም የጠበቀ፣ የቅርብ የግል ወዳጅ ልታደርገው ትችላለህ፡፡ የአንተ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ወዳጅነት ልናደርግና ሊበለጽግ ልክ እንደተፈጥሮአዊ ወዳጅነት ሁል ጊዜ እና ኃይል ያስፈልገዋል፡፡

እኔ የማበረታታህ ጊዜህንና ጉልበትህን ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከር ትኩረትህን ለእርሱ በመስጠት ቃሉን በማንበብና በማሰላሰል በመናገርና እርሱን በመስማት ወዳጅነትን አሳድግ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነትን ለማጠናከር በሕይወትህ ጊዜህንና ጉልበትህን በመጠቀም እድል ስጥ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon