የእግዚአብሔር ድምፅ ከቃሉ ጋር ይስማማል (አይጋጭም)

የእግዚአብሔር ድምፅ ከቃሉ ጋር ይስማማል (አይጋጭም)

አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልብ ሰወርሁ፡፡ መዝ 119÷11

አንድ ወቅት ቁጭ ብዬ መጽሐፍ ስጽፍ እግዚአብሔር እየተናገረኝ እንደሆነ ተሰማኝ እንዲህ ስል ‹‹ለጥቂት ደቂቃዎች ቆየኝ›› የሚል ነበር፡፡ ለጥቂት ሰዓታት ጠበኩና ስልክ መደወል ጀመርኩ፡፡ ጌታ በትህትና ‹‹እኔ የስልክ ጥሪ እንድታደርግ አልነገርኩሽም›› አለኝ እኔ የነገርኩሽ እንድትጠብቂኝ ነው›› የሆነ ነገር ለመስራት ያለኝ ፍላጎት የተለመደ አልነበረም፡፡ ብዙ ሰዎች ዝግና ፀጥ ብሎ በትዕግስት ሰውን ነገሮችን ወይም እግዚአብሔርን እንኳ ለመጠበቅ ትዕግስት የላቸውም፡፡ ዝም ብሎ ለሰዓታት ስጠብቅ ጌታ ለእኔ መናገር ጀመረ ስል መላዕክት ድንገት ያልጠበኩት ነገር ነው፡፡ ወደተለያዩ የመጽሐፍ ጥቅሶች ከእግዚአብሔር ቃል በመላዕክት ኃይልና መገኘት በተመለከተ ትንሽ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያክል ትምህርት አጠናቀኩ፡፡ እግዚአብሔር ለሚያደርገው ነገር ሁሉ ምክንያት አለው፡፡ ስለዚህ እኔ አምናለሁ ስለመላዕክት በእኔ ጉዳይ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ እንዳውቅ ፈልጎ እንደነበር ነው፡፡ ከዚህ በፊት ለብዙ ጊዜ ያልተማርኩት ጉዳይ ነበር፡፡

በትክክል እግዚአብሔ ስለመላዕክት ጉዳይ ተናገረኝ ወይስ በአእምሮዬ ውስጥ ተቀናበረ መረዳት ነው የሚለው ሊገርምህ ይችል ይሆናል፡፡ መልሱ ሙሉ ሠላም ለሰማሁት ነገር ይሰማኛል፡፡ ትክክለኛነት ሰሜት በውስጥ ይሰማኛል፡፡ መንፈስ ቅዱስ መልዕክቱ ከጌታ መሆኑን ሲያረጋግጥልኝ ከእግዚአብሔር ቃል ሲስማማ ከእግዚአብሔር ድምፅ መስማቴን አረጋግጣለሁ፡፡

የእግዚአብሔንና ሌላ ድምፅ የሰማሁበት ጊዜያት ነበሩ፡፡ በእርግጥ የእግዚአብሔር ድምፅ እንዳልነበሩ አውቃለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ለይተን ለማወቅም ሆነ የሌላ ድምፅን ለመለየት በቃሉ ብርሃን መለየት አለብን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔርን ቃል ካጠናህ የእግዚአብሔርን ድምፅ ትለያለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon