የእግዚያብሔር ፍቅር ታላቅ ነው

የእግዚያብሔር ፍቅር ታላቅ ነው

ከፍታም ይሁን ጥልቀት፣ ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም። – ሮሜ፡8፡39

አለአግባብ መጠቀም ማለት አንድን ነገር ከሚፈለገው አገልግሎት ውጪ መጠቀም ማለት ነው፡፡ አልአገባብ የመጠቀም ውጤቱ እጅግ በጣም አደገኛና ጥፋቱም ዘላቂነት ያለው ነው፡፡ ብዙዎችም ከዚህ ጉዳት ለማገገም ይቸገራሉ፡፡

በጣም የተለያዬ ህገወጥ ተግባራት አሉ፤ ለምሳሌ የጾታ፤የስነልቦና፤የቃላትና አካለዊ ጥቃት ናቸው፡፡ ቅርፁ ምንም ይሁን ምን ውጤቱ ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ በአግባቡ ከመንቀሳቀስ ያግዳችኋል የእግዚያብሔርን መንግስት ሰላም፤ ፍቅርና ደስታን ከመለማመድም ይከለክላችኋል፡፡

ይህንን በጣም ነው የምረዳው ምክንያቱም በልጅኔት እንዲህ አይነት ጥቃት ደርሶብኛል፡፡ ደስ በሚል ሁኔታ የጥቃትን ኃይል ብቻ አይደለም የማውቀው ነገርግን የእግዚያብሔርን ታላቅ የሆነ የፍቅሩን ኃይል በሚገባ አውቃለሁ፡፡ ከእግዚያሔር የፍቅር ኃይል የተነሳ ከዚህ በፊት የደረሰብኝ ጥቃትን እረስቼዋለሁ፤ ወደፊቴንም ሊያበላሽብኝ አይችልም፡፡

ጥቃት ተፈፅሞባችሁ ከሆነ የእግዚያብሔርን ፍቅር አስቡት ከእርሱ ፍቅር ምንም ሊለያችሁ አይችልም ካለፈው ዘመን ሁኔታችሁ ፈፅሞ ነፃ አውጥቷችኋል ፤ የእርሱንም ዓላማ እንድትኖሩ በፍቅሩ ጠርቷችሃል፡፡
ከኢየሱስ ጋር አዲስ የህወት ተስፋ አለ። ዛሬ ፍቅሩን መቀበል ትፈልጋላችሁ?


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ባለፈው ዘመን በደረሰብኝ ችግር ምክንያት ለህይወቴ ካዘጋጀኸው ከዓላማ መዘግየት አልሻም። በጥቃት ውስጥ ማዳንህንና ነጻነትህን እንድረዳ በፍቅርህ አጨናንቅኝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon