የጸሎት ትርጉምህን ቀይር

የጸሎት ትርጉምህን ቀይር

ሳታቋርጡ ጸልዩ – 1 ተሰ 5:17

“ያለ ማቋረጥ ጸልይ” የሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ሀረግ ሰምታችሁ ታዉቃላችሁ? ለብዙዎች ይህ ድምጽ ተስፋ አስቆራጭና የማይቻል ይመስላል፡፡ እንዴት ነዉ አንድ ሰዉ ራሱን አቀርቅሮ፣ በጉልበቱ ተንበርክኮ በቀን ሀያ አራት ሰዓት መጸለይ የሚችለዉ?

የበለጠ ግልጽና ተግባራዊ የሆነ የጸሎት ትርጉም/ፊቺ ያስፈልገናል፡፡ ብዙዉን ጊዜ ስለ ጸሎት ያለን እይታ ወደ አንድ የተወሰነ ቦታ ሄደን ብቻችንን ሆነንና ሌላዉን ዓለም ረስተን የምናከናዉነዉ ተግባር የሚመስል ነዉ፡፡

ሀሳብን ወደ እግዚአብሔር መስደድ በዝምታ ዉስጥ እንዳለ ጸሎት ስለመሆኑ ልብ ብለህ ታዉቃለህ? እዉነት ነዉ! ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ሳታቋርጡ ጸልዩ ሲል ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ሁል ክፍት ሁን ማለቱ ነዉ፡፡ ያ ማለት የሁለት ሰዓት ጸሎት ሊሆን ይችላል አሊያም በዉሎህ የእርሱ መገኘት እንዲኖር ጠይቆ መዋልንም ያካትታል፡፡

እግዚአብሔር ጸሎትን ዉስብስብ አድርጎ አልሰራዉም፤ እርሱ ጸሎትን የየእለት ዉሎአችን አንዱ አካል እንዲሆን አስቦ ነዉ የሰራዉ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ስለጸሎት ያለህን ግንዛቤ ለዉጠህ ከሚወድህ አምላክ ጋር በሚኖርህ ንግግር የሚመጣዉን ደስታ ተለማመድ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! የጸሎት ትርጉሜን እንድቀይር እርዳኝ ቀንም ሆነ ማታ ከአንተ ጋር የምነጋገርበትን የጸሎት መንገድ አሳየኝ፡፡ ሁል ጊዜ አብረኸኝ ስላለህ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon