ወንድሞች ሆይ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፣ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፣ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ፡፡ ገላ 5 13
አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ጉዞ ውስጥ ሳናውቅ በምናደርገው ነገሮች ሰዎችን እንጎዳለን፡፡ እኔ በባሕሪዬ ግልፅና ፊት ለፊት የሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ ይህ ደግሞ ጥሩ ባሕሪ ነው፡፡ ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በማደርገው ቅርበትና ንግግር የእነርሱን ስሜት ለመረዳት መማር አለብኝ፡፡ አንድ ወቅት ላይ የተናገርነው በሌላ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተገቢ ያልሆነ ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥ እኛ በክርስቶስ ነፃ የወጣንና እራሳችን የመሆን መብት አለን፡፡ ነገር ግን የፍቅር ሕግ ከእኛ የሚፈለገው የእኛ ነፃነት በዓለመኝነት ወይም በራስ ወዳድነት በር እንዲከፍትብን አይፈቅድም፡፡
የወደድነውን ወይም የተሰማንን ነገር ዝም ብለን ለመናገርም ሆነ ለማድረግ ያለንበት ሁኔታዎች ይወስኑናል፡፡
የወደድነውን ወይም የተሰማንን ነገር ዝም ብለን እንዳንናገር ወይም እንድናደርግ ሁኔታዎች ይገድቡናል፡፡ ለምሳሌ ለረዥም ጊዜ እየታመሙ ካሉ ሰዎች ጋር እያወራ ካለህ ሁልጊዜ እንዴት ደስ እያለህ እንዳለህ ልታወራቸው ጥሩ ጊዜ አይደለም ወይም ደግሞ ስራውን ካጣ ሰው ጋር እያወራህ ከሆነ ያለኸው እንዴት በሥራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ እንዳገኘህ ለመናገር ጥሩ ጊዜ አይደለም፡፡ ኢየሱስ የሞተው በነፃነት በደስታ እንድንኖር ነው፡፡ ስለሆነም እርስ በርሳችን በፍቅር እንድናገለግል ግልፅ አድርጎ ያዘናል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ሌሎችን ስታስደስት እራስህ የበለጠ ደስተኛ ትሆናለህ፡፡