ይለውጥሃል

የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።። (1 ሳሙኤል 10፤6)

የእግዚአብሄርን ድምጽ መስማት መቻል እርሱን በማወቅ እና በመንፈሱ መሞላት፣ ነገር ግን በመንፈስ የተሞላ ሕይወት ብቸኛ ማስረጃ አይደለም ። ሌላው ቀላል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ያለውን ኃይል የሚያሳይ ማስረጃ የተለወጠ የሰው ሕይወት ነው ። ኢየሱስ በቀረበበት ወቅት ጴጥሮስ አይሁድን ስለፈራ ሦስት ጊዜ ክዶታል (ሉቃስ 22 56

– 62 ን ተመልከት) ፤ ነገር ግን በጰንጠቆስጤ ቀን በመንፈስ ቅዱስ ከተሞላ በኋላ ቆሞ በጣም ድፍረት የተሞላበት መልእክት ሰበከ የጴጥሮስ ስብከት ያስገኘው ውጤት በዚያ ቀን በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ የተጨመሩ ሦስት ሺህ ነፍሳት ናቸው (የሐዋርያት ሥራ 2 14– 41 ተመልከቱ) ። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጴጥሮስን ወደ ሌላ ሰው ቀይሮታል፤ በጣም ደፋርና ጨርሶ የማይፈራ ሰው ሆነ።

በዚያ ቀን በድፍረት የቆመው ጴጥሮስ ብቻ አልነበረም ። አሥራ አንዱም የቀሩት ደቀ መዛሙርትም ተመሳሳይ ነገር አደረጉ ።ኢየሱስ ከትንሣኤው በኋላ ወደ እነርሱ ሲመጣ ሁሉም አይሁዶችን በመፍራት በኋላ በተዘገ በር ተደብቀው ነበር (ዮሐንስ 20 19 እስከ 22ን ተመልከት።) በድንገት በመንፈስ ቅዱስ ከተሞሉ በኋላ ሁሉም የማይፈሩና ደፋሮች ሆኑ።

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በዓመታት ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ሰዎች በላቀ ሁኔታ ቀይሯል፡፡ በዛሬው ክፍል ላይ የተጠቀሰው ቃል ሳኦልን ለውጦታል ። ጴጥሮስን ቀይሮ ሌሎቹንም ደቀ መዛሙርት ቀይሮአቸዋል፤አሁንም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በቅንነት የሚፈልጉትን መቀየሩን ይቀጥላል ። ዛሬ ምላሽህ መለወጥ ያስፈልግሃል? መንፈስ ቅዱስን ጠይቁ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ ዛሬ፡ ለመለወጥ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያስፈልግሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon