ይረዳሃል

ይረዳሃል

እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፡- አትፍራ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና፡፡ ኢሣ 41 13

ሕይወታችንን ምን ያህል ጥሩ አድርገን እንደምናስብበት ብቻ ሳይሆን እውነታው በእያንዳንዱ ነገር ውስጥ የእግዚአብሔር እርዳታ በጣም አስፈላጊ መሆኑ ነው፡፡ እያንዳንዱ እርዳታ በእያንዳንዱ የዕለት ኑሮአችን ውስጥ የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፈልጋል፡፡

ብዙውን ጊዜ ምን ያህል እርዳታ እንደሚያስፈልገን ለማወቅና ለመርዳት ረጅም ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ የሚያስፈልገንን ሁሉ ለእራሳችን ማድረግ እንደምንችልና ምንም ዓይነት እርዳታ እንደሚያስፈልገን እራሳችንን ለማሳመን እንፈልጋለን፡፡ ይሁን እንጂ ጌታ መለኮታዊ እርዳታ ሲልክልን ስለዚህ እርዳታ መፈለግ አለብን፡፡ ኢየሱስ ራሱም ያለማቋረጥ ስለ እኛ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት ያማልዳል፡

፡ (ዕብ 7 25፣ ሮሜ 8 34 ተመልከት) እነዚህ የእግዚአብሔር እርዳታና ጣልቃ ገብነት በቀጣይነት በሕይወታችን እንደሚያስፈልጉን ያረጋግጡልናል፡፡ በመሠረቱ እኛ ሙሉ በሙሉ በእራሳችን ሕይወታችን በሥርዓት ማስከድ የማንችል ተረጅዎች ነን፡፡

እኛ ሕይወታችንን መምራት የምንችል ከመሰለንም ለጊዜው ቢሆንም ግን ወዲያውኑ ወይም በኋላ የሆነ ነገር ይገጥመንና ነገሮች መበላሸት ይጀምራል፡፡ እኛ በራሳችን ብርታት ያለ መለኮታዊ እርዳታ የምንቀሳቀስ ከሆነ፡፡

ብዙውን ጊዜ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ በሕይወታችን ይጓዛል፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታ እስካልመጣ ድረስ አስቸጋሪ ሁኔታም የሚመጣው በትዳር መፍረስ፣ የሚወዱት ሰው መሞት፣ የሥራ ማጣት እነዚህ የመሳሰሉት ነገሮች ለእኛ በጣም የሚያስፈልጉን ነገሮች ናቸው፡፡ ውሎ አድሮ በመጨረሻ ግን እኛ ሁላችን ትክክለኛ ፍላጎታችንን ወደ መረዳት ላይ እንደርሳለን፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያሰበውን ዓይነት ሕይወት፡- በጽድቅ የተሞላለ፣ የሠላምና የደስታ (ሮሜ 14 17 ተመልከት) ለመኖር ከፈለግን እርዳታ እንደሚያስፈልገን ማመንና ያየን እርዳታ ከመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲረዳን ከላከልን መቀበል አለብን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለሕይወትህ ለሚያስፈልግህ እርዳታ እንደሚያስፈልግህ እመንና መንፈስ ቅዱስ እንዲረድህ ታመነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon