ይቅርታን እንጂ ኩነኔን አትቀበሉ

ይቅርታን እንጂ ኩነኔን አትቀበሉ

ኃጢያታችንን ብንናዘዝ ኀጢያታችንን ይቅር ሊለን፣ከዐመጻ ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው፡፡ – 1 ኛ ዮሐ  1፡9

በእያንዳንዷ የህይወታችን ቀን ይቅርታ ያስፈልገናል፡፡መንፈስ ቅዱስ ሀጢያትን እንድንለይ በልባችን የማንቂያ ደውል አስቀምጧል፣ ሁልጊዜ ከሀጢያት ለማንጻት እና ከእግዚአብሔር ጋር በትክክለኛ ጎዳና እንድንጓዝ  የኢየሱስን ደም ሀይል ሰጥቶናል፡፡

ነገር ግን በኩነኔ ከተሸነፍን ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን እንችላለን፡፡ኢየሱስን ለእኛ እንዲሞት ነው የላከው፥ ለሀጢያታችን ዋጋን እንዲከፍል፡፡ሀጢያታችንን እና ኩነኔያችንን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሸክሞታል (ኢሳ.53 ይመልከቱ) ።

እግዚአብሔር የሀጢያትን ቀንበር ከእኛ ላይ ሲሰብር፣ የጥፋተኝነት ስሜቱንም አስወግዶታል፡፡ሀጢያታችንን ሁሉ ይቅር ለማለትና በቀጣይነት ጽድቅ ካልሆነ ነገር ሁሉ ሊያነጻን ታማኝ ነው (1ኛ ዮሐ.1፡9) ፡፡

ዲያቢሎስ ኩነኔ እና ሀፍረት ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ቀርበን ይቅርታ እንዳንቀበል እና ጥብቅ ህብረትን ከእርሱ ጋር እንዳናደርግ እንደሚያግደን ያውቃል፡፡

ስለራሳችን መጥፎ ስሜት መሰማት ወይም እግዚአብሔር እንደተናደደብን ማሰብ ከርሱ ቀረቤታ ይለየናል፡፡እርሱ መቼም አይተዋችሁም፣ ስለዚህ በኩነኔ የተነሳ ከርሱ አትራቁ፡፡ይቅርታውን ተቀበሉና ከእርሱ ጋር ተራመዱ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ያ ወቀሳ ከአንተ ዘንድ እንዳልሆነ ስላሳየኸኝ አመሰግናለሁ፡፡ዛሬ ይቅርታህን እቀበላለሁ፡፡ከሀጢያት አነጻኸኝ ከአንተ ጋር በትክክለኛ መንገድ አንድቆም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon