ይቅርታ፡ የእውነተኛ ሰላምና ደስታ መንገድ

ይቅርታ፡ የእውነተኛ ሰላምና ደስታ መንገድ

ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ ምንም ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፥ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፥ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፥ እርሱ ለማያመሰግኑ ለክፉዎችም ቸር ነውና። – ሉቃ 6፡35

ከጥቂት አመታት ቢፊት አንድ ሰው በአገልግሎታችን ንግድ ስለሚሰራ አንድ ሰው ነገረኝ፡፡ ወዳጄ እኛ ባልንበት ሆቴል ተገኝቶ ተጎናችን ስለ እኔ የሚደረገውን ውይይት ይሰማ ነበር፡፡ ሁለቱም ስለ እኔ የሚያወሩት ነገር መልካም አልነበረም፡፡

በመጀመሪያ በጣም ተናድጄ ስለነበር ከዚህ በኋላ ከእኛ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደማይኖረን ልነግረው ፈልጌ ነበር፡፡ ነገር ግን በዛው ምሽት መንፈስ ቅዱስ “እነዚህን ነገሮች ልታደርጊ አትችይም” በማለት ተናገረኝ፡፡ “የምታስተምሪውን  ነው ማድረግ ያለብሽ” ብሎ ተናገረኝ፡፡ “ስጦታ ገዝተሽ በመስጥት በእነዚህ ሁሉ አመታት ስለሰጠው አገልግሎት ምን ያህል እንደምታደንቂው ትነግሪዋለሽ አለኝ፡፡”

ቀላል አልነበረም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠኝን ምሪት የምታዘዝበትንና ለዚህ ሰው በረከት የምሆንበትን ጸጋ ሰጠኝ፡፡ ስለ ሁኔታው በጣም የማስታውሰው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ያለኝን ነገር መታዘዝ በጀመርኩበትና ለዚህ ሰው መልካም ነገር ማድረግ በጀመርኩበት ቅጽበት በማደርገው ነገር በጣም ደስተኛ መሆን ጀምሬ ነበር፡፡

የጎዱንን ሰዎች በርህራሄ ማየት ስንጀምር የእግዚአብሔር ደስታ በነፍሳችን ስለሚሞላ በውስጣችን የሚፈጠር ታላቅ ድግስ አለ፡፡ ዛሬ ይቅር የምትሉትና መልካም ነገር የምታደርጉለት ሰው ማን ነው? ይቅርታ በማድረግ ወደ እውነተኛ ሰላምና ደስታ የሚወስደውን መንገድ ተከተሉ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

አምላክ ሆይ ፣ ቃልህን ለመታዘዝ እና ለሚጎዱኝ መልካም ለማድረግ ጸጋህን እፈልጋለሁ ፡፡ ይቅር ማለት እና መባረክ ስጀምር ነፍሴን በሰላምና በደስታ እንደምሞላ አውቃለሁ ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon