ጥርጣሬን ተጠራጠረው

ጥርጣሬን ተጠራጠረው

ሁሉን ይታገሣል ፣ ሁሉን ያምናል ፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል ፣ በሁሉ ይጸናል፡፡ – 1ቆሮንቶስ 13፡7

1 ቆሮ 13 ፡ 7 ሰዎችን መወደድ ምን ማለት እንደሆነ ያስገነዝበናል ፡፡ ይህን ጥቅስ መታዘዝ ለኔ ፈታኝ መሆኑን በታማኝነት እነግራችኋለሁ፡፡ ሳድግ ሰዎችን እንድጠረጥር እና እንዳላምን ተምሬኣለሁ፡፡ ነገር ግን ስለፍቅር ባህሪያት ሳሰላስል እና ፍቅር ሁሌ እንደሚያምን ስገነዘብ አዕምሮዬን በአዲስ መልክ እንድቃኝ አድርጎኛል፡፡

ጥርጣሬ የጤናማ ግንኙነት ጥራትን ተቃርኖ የሚቆም ነገር ነው፡፡ መደገፍ እና እምነት ግንኙነቶች ማደግ እና በህይወታችን ላይ ደስታ ሊሚያመጡ በሚችሉበት ከፍታ ሲያሳድግ ጥርጣሬ ግን ግኑኝነትን ያሰናክላል ያጠፋልም፡፡

እውነት ነው ፤ ሰዎች ፍፁም አይደሉም አንዳዴም በሰዎቹ እምነታችንን ለጥቅማቸው ሊመነዝሩት ይችላሉ ነገር ግን በሰዎች ውስጥ ሁሌም ከከፍት ይልቅ በጎውን ብቻ መመልከታችን ጥቅሙ የላቀ ነው፡፡

ከጥርጣሬ ጋር የምትታገሉ ከሆናችሁ እና ሀሳባችሁ ወደ ጠማማነት አቅጣጫ የሚመራችሁ ከሆን አስደናቂው መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ሆኖ እንዳታስቡ ሊያደረጋችሁ መሆኑን ልብ አድርጉ፡፡ ተጠራጣሪ ሀሳባችሁን ወደ ፍቅር ሀሳብ እንዲቀይርላችሁ ጠይቁት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ዘወትር ተጠራጣሪ እና ሰዎችን አለማመን ግኑኝነቴን አጥፊ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ልቤን በሁኔታዎች ሁሉ ለሰዎች እንዱት መክፈት እና ማመን እንዳለብኝ አስተምረኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon