ፈጽሞ ብቻህን አይደለህም!

ፈጽሞ ብቻህን አይደለህም!

በፊትህም የሚሄድ እርሱ እግዚአብሔር ነው ከአንተ ጋር ይሆናል፥ አይጥልህም፥ አይተውህም አትፍራ፥ አትደንግጥ አለው። – ዘዳ 31:8

ዘንና ብቸኝነት ሰዎችን የሚገጥሟቸዉ ዋነኛ ችግሮች ናቸዉ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ሁለቱም አብረዉ ይሄዳሉ ምክንያቱም ሰዎች ብቸኛ ስለመሆናቸዉ ያዝናሉና፡፡ በአገልግሎታችን ከብቸኝነት ጋር ከሚታገሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የጸልዩልን ጥያቄ እንቀበላለን፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ብቻችንን እንዳልሆንን በግልጽ ይነግረናል፡፡ እርሱ ነጻሊያወጣን፣ ሊያጽናናንና ሊፈዉሰን ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን የሚያሳምም ማጣት ሲደርስባችሁ ይህንን ቀላል እዉነት የሚያይ ዓይን ታጣለችሁ፡፡

ሳይጣን ብቻችሁን እንደሆናችሁ እንድታምኑ ይሰልጋል፡፡ እናንተ የሚሰማችሁን ማንም እንደማይረዳ እንድታምኑ ይፈልጋል ነገር ግን እርሱ እኮ ውሸታም ነዉ፡፡ ከእግዚአብሔር አብሮነት በተጨማሪ በአእምሮም ሆነ በስሜት የምታልፉበትን ሁኔታ የሚረዱ በጌታ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች አሉላችሁ (2ቆሮ 13፡4ን ተመልከት)፡፡

ምንም ይግጠምህ ምንም አሁንም ብቻህን አይደለህም ፈጽሞም ብቻህን አትሆንም፡፡

ምንአልባትም ስትጎዱና የማጣት ህመም ነፍሳችሁን ሲወር ላትረዱት ትችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህንን እዉነት እወቁ አጥብቃችሁም ያዙ፡፡ እግዚአብሔር ይወዳችኋል ደግሞም ለእናንተ መልካም ፍጻሜ አለዉ ስለዚህ ለቅሶአችሁ ወደ ሀሴት እንዲቀየር በእርሱ ተስፋ አድርጉ እመኑትም (ት. ኢሣ 61፡1-3ን ተመልከት)፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

አባት ሆይ! በሐዘኔና በብቸኝነቴ ዉስጥ እዉነቱን ሁሌ ማየት አልችልም ግን አንተ ፈጽሞ እንደማትተወኝ አዉቃለሁ፡፡ አንተ አጠገቤ እንደሆንክ እንዳስታዉስ እርዳኝ አንተን የበለጠ እንፈልግ የሚያበረታቱኝን ክርስቲያን ጓደኞችም ስጠኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon