ፍርሃት ወደ ውስጣችሁ እንዲገባ አትፍቀዱ

ፍርሃት ወደ ውስጣችሁ እንዲገባ አትፍቀዱ

እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። – ዘፍ 12፡1

መጽሐፍ ቅዱስ ከግል ጉዳዩ ባለፈ እግዚአብሔርን ስላመነ አብርሃም ስለሚባል ሰው ይነገረናል፡፡ እግዚብሔር ከቤታችን፣ ከቤተሰባችንና ከለመድነውና ተመችቶን ከምንኖርበት ሁኔታ ውስጥ ወጥተን በቅጡ ወደማናውቀው ወደ ሌላ አገር እንድንሄድ ቢነገረን ምን ዓይነት ስሜት ነው የሚፈጠርብን? ፍርሃት? እግዚአብሔር ለአብርሃም እንዲያደርግ የነገረው እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይለው የነበረው ነገር አትፍራ ነበር፡፡

በዙ ጊዜ አንድን ነገር ለማድረግ ፍርሃታችን እስኪጠፋ ድረስ መጠበቅ ያለብን ይመሰናል፡፡ ነገር ግን በዚህ መልክ የምናደርግ ከሆነ ለእግዚአብሔርም፣ ለሌሎችም ለራሳችንም በጣም ጥቂት ነገር ነው ማድረግ የምንችለው፡፡ አብርሃም ከፍርሃቱ ባሻገር በእምነት እርምጃ መውሰድና እግዚአብሔርን መታዘዝ ነበረበት፡፡ አብርሃም ለፍርሃት ጉልበቱን አንበርክኮ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር እንዲሆን የፈለገውን ፍጻሜ – የሕዝብ ሁሉ አባት የመሆንን ፍጻሜ መፈጸም አይችልም ነበር፡፡

ፍርሃት ወደ ውስጣችን እንዲገባ መፍቀድ እግዚአብሔር ለሕይወታችን ያለውን ድንቅ ዓላማ ያዛባል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር እንድታደርግ የሚፈልገውን ነገር አድርግ፡፡ ልክ እንደ አብርሃም በፍርሃት ብታደርጉት እንኳ ብድራቱ ታላቅ ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በፍርሃት ውስጥ በታዘዘህ ጊዜ አንተ ለአብርሃም ታማኝ ነበርክ፡፡ ስለዚህ እኔም ፍርሃትን ተቋቁሜ እንዳደርገው የፈለከውን ነገር ሁሉ ለማድረግ ወስኛለሁ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon