ሰዎችን በሚገባ ያዝ

ለድሆች ጩኸት ጆሮውን የሚዘጋ ሁሉ ራሱ ይጮኻል ደግሞም አይሰማም። (ምሳሌ 21:13)

የዛሬው ጥቅስ የሚያመለክተው ለተቸገሩ ሰዎች ትኩረት የማልሰጥና እነሱን ለመርዳት ምንም የማላደርግ ከሆነ፣ እግዚአብሔርም ስፈልገው እና ለእርዳታ ስጣራው ላይመልስልኝ ይችላል ማለት ነው።

ለሰዎች ጥሩ መሆን ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን አልፈው እስከ ማህበረሰቦቻችን ይዘልቃል። በሴንት ሉዊስ ቤት አልባ የሆነ ሰው አማካይ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነው የሚል አንድ ስታትስቲክስ አንድ ጊዜ ማንበቤን አስታውሳለሁ። በከተማዬ ውስጥ!

ከሃያ ዓመታት በፊት ለዚያ የሰጠሁት መልስ ምናልባት “ያ በእውነት አሳዛኝ ነው” የሚል ነበር። አሁን ግን እንደዚያ ያሉ እውነታዎችን አውቄ “ስለዚያ አንድ ነገር አደርጋለሁ!” እላለሁ። ሰዎች “ጆይስ እንዲህ ማለት ለአንቺ ቀላል ነው፤ ትልቅ አገልግሎትና መርዳት የሚችሉ ብዙ ሰዎች ማግኘት የምትችይበት እድል አለሽ” ሊሉኝ ይችላሉ። በአገልግሎት የምናገኛቸው አንዳንድ ሀብቶች ላይኖሩህ ይችላሉ፣ ነገር ግን እኔ እኔ እንደማደርገው የመጸለይ ተመሳሳይ ችሎታ አለህ። ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ለመርዳት ለሚሞክሩ አካላት ስጦታ መስጠት ትችላለህ። ሄደህ ትንሽ ጊዜ በፈቃደኝነት ማገልገልም ትችላለህ። ሁላችንም በእውነት ከፈለግን አንድ ነገር ማድረግ እንችላለን።

ብዙ ጸሎቶቻችን መልስ አማያገኙት ደግሞም አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት የሚሳነን በዙሪያችን ላሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምህረትን ወይም ርህራሄን ስለማናሳይ ነው ብዬ አምናለሁ። እውነታው መልካም በመሆናችን ብቻ እጅግ የላቀ መከርን መሰብሰብ እንችላለን! ሰዎችን በጥሩ ሁኔታ መያዛችን ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ ነው። መቼም ተረስተህ ወይም ተበድለህ የምታውቅ ከሆነ ያ ምን ያህል እንደሚያም እንደሆነ ታውቃለህ። ውጤታማ ጸሎት መጸለይ ከፈለግህ – የእግዚአብሔር ጆሮዎች ወደ አንተ ድምጽ እንዲመለሱ ከፈለግህ – ሰዎችን በጥሩ ሁኔታ መያዝ እና ለእነርሱ መልካም መሆን አለብህ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ልታደርጋቸው ከምትችላቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል አንዱ የአንተን ያህል እድል ያላገኘን ሰው መርዳት ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon