በሃዘን ወቅት ስሜትን መቆጣጠር

በሃዘን ወቅት ስሜትን መቆጣጠር

ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤ – መዝሙ42፡5

በጣም ብዙ ጊዜ ሃዘን የደረሰባቸው ሰዎች የስሜት አለመረጋጋት ያጋጥማቸዋል ፤ ይሁን እንጅ ሃዘናቸውን በሆነ መንገድ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ በማንጠብቀው ሰአት ምርር ብለው ያለቅሳሉ፤ እንባቸውንም በማፍሰስ በውስጣቸው ያዘሉትን ምቾት ማጣትና የስሜት መጎዳትን ያንፀባርቃሉ፡፡ ግራ መጋባት፣ ፍርሃት፣ ድብርት እና በስሜት ማዕበል መናጥ የተለመዱ ክስተቶች ናቸው፡፡ በዚህ አይነት ክስተቶች ወቅት ወደ መዝሙረዳዊት መፅሃፍት መመልከት እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው ብየ አስባለሁ፡፡

በመዝሙር 42፡5 ላይ ዳዊት የድብርት ስሜት ሲጫጫነው ስሜቱን ወደ ውስጥ ከማስተናገድ ይልቅ ሲቃወመው እንመለከታለን፡፡ ስለተሰማው ስሜት ገለፆል ነገር ግን በስሜቱ ውስጥ ላለመኖር ውሳኔ አደረገ። ከዚያ ስሜቱ ይልቅ እግዚያብሔርን ሲያመልክና ሲያመሰግን እንመለከታለን፡፡
አሳዛኝ ክስተቶች በሚከሰቱበት ወቅት ብዙዎቻችን አሳዛኝ ስሜቶችን አስተናግደናል፡፡ ለማዘን ለራሳችን ግዜ ልንሰጥ ይገባል፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ በምናልፍበት ወቅት እግዚያብሔር ሊያፅናናንና በርትተን ማለፍ እንድንችል ፀጋን ሊሰጠን ይፈልጋል፡፡ በእግዚብሔር ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ከገጠማቸው ሁኔታዎች በጥበብ መውጣት የሚችሉበትን ኃይል ይጎናፅፋሉ፡፡

በአሁኑ ሰአት በህይወታችሁ ውስጥ ባጋጠማችሁ ችግር ምክንያት በሐዘን ውስጥ ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ልነግራችሁ የምፈልገው አዲስ የሆነ ጅማሬ ከፊታችሁ እንዳለ እንድታውቁ ነው፡፡ ልክ እንደ ዳዊት እግዚያብሔርን አመስግኑት ደግሞም በእርሱ ታመኑ ሰይጣን ሊጎዳችሁ ብሎ ያደረገውን እግዚያብሔር ለበጎ ይቀይረዋል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሐየር ሆይ በሃዘን ባለሁበት ወቅትና ሰዓት እንኳ አንተን ማመስገንና በአንተ ላይ መደገፍን እሻለሁ፡፡ ልክ በሮሜ 8፡28 ላይ እንደሚናገረው ሁሉንም ነገር ለበጎ ትቀይረዋለኽ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon