በእሳት መጥራት

በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና አምድ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ፡፡ ዘፀ – 13÷21

መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የእግዚአብሔር እሳት እንዴት በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮቻችን እንደሚሠራ በተለያዩ የመጽሐፍ ክፍሎች ይዘረዝራል፡፡ የተሻለውን የእግዚአብሔርን ነገር ብንፈልግ የእግዚአብሔርን በእሳት የማጥራት ሕይወት ለመኖር ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ በውስጣችን ወርቅ (ጥሩ የሆነ ነገር) በውስጥ ሕይወታችን አለን፡፡ ነገር ግን ያልተጠሩና ሊወገዱ የሚገቡ ነገሮችም አብሮ አሉን፡፡ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር መልካምነት መደሰት ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ በእሳቱ በተከታታይ ለመሠራት ጉጉት አለው፡፡ የእግዚአብሔር እሳት በሕይወትህ ሲመጣ ለውጥን የሚያመጣ ነበልባል እንደሆነ ሁልጊዜ አስታውስ፡፡ እሳቱ ከሕይወታችን ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ አያደርግም፡፡ እንዲሁም ደግሞ እሳቱ እንዲያጠፉንም አያደርግም፡፡ እርሱ ከምንችለው በላይ እሳቱ እንዲያይልብንም አያደርግም፡፡ በሕይወታችን ሁሌ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ የሚመስና ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀላል የሚመስሉ ገጠመኞች ይፈራረቁብናል፡፡ ጳውሎስ ይህንን ጊዜያት ሲገልጽ በሁሉም እራሱን ለማስለመድና ከሁለቱ በአንዱ ለመደሰት የምችልበት እንደተማረ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ፍጹም እንደሆነና ሁሉን ነገር ለመልካም እንደሚሆን ተምሮአል፡፡

እኛም ልክ እንደ እርሱ ምርጫችንን ማድረግ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔርን እሳት መቋቋማችን በእኛ ሕይወት እንዳይነድ ከማድረግ መከልከል አንችም፡፡ መቃወማችን እለቱ በሕይወታችን አይሎ እንዲሠራ ማድረግ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር እሳት የሚመጣው ጥቅም የሌለውን ነገር ከሕይወታችን ለማቃጠልና በሕይወታችን ብሩህ ሆነው የምሰራውን በመተው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ስናጠና እና በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ስንፈርድ ይሰማል፡፡ በሌላ ጊዜያት የእግዚአብሔር እሳት ደስ በማያሰኝ ሁኔታ በማረጋጋት እንድቆይና እግዚአብሔራዊ ባሕሪይ እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ በማንኛውም ጊዜ አንዳንድ ነገሮች አስቸጋሪ ቢሆኑም ለእግዚአብሔር ክብር እስከኖረን ድረስ ሽልማቱ በተገቢው ጊዜ ይሆናል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በምታልፍባቸው ነገሮች ውስጥ ከነገሮቹ መሸሽ የለብህም ልትፈራቸውም አይገባህም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon