« …የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል። ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና» (መዝ.37፡23 – 24)።
እግዚአብሔር በእያንዳንዱ የህይወታችን እርምጃ ውስጥ በሥራ ላይ ነው! ይህም ማለት እኛ ብቻችን አይደለንም። ስንወድቅ መልሶ የሚያነሳንና እንደገና ወደ ፊት እንድንራመድ የሚያበረታታን ነው። ማንም ሰው አንዳንድ ስህተቶችን ሳያደርግ በእግዚአብሔር መመራትን የተማረ የለም፣ ነገር ግን አንተ ሳታደርጋቸው በፊት እግዚአብሔር እንደሚያውቃቸው አስታውስ። እግዚአብሔር በውድቀታችንና በስህተቶቻችን እግዚአብሔር አይደነቅም። እንደጉዳዩእውነትነትእግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ቀናቶቻችን አንዳቸውም ወደመሆን ከመምጣታቸው በፊትም ጭምር በመጽሐፍቱ ተጻፉ (መዝ. 139፡16)። እግዚአብሔር በአንተ ደስ እንደሚለው አስታውስና በእያንዳንዱ እርምጃዎችህ በሥራ ላይ ነው። ወድቀህ ከሆነ እርሱ ወደ ላይ ያነሳሃል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ስለምናነባቸውና ስለምናደንቃቸው ስለሁሉም ታላላቅ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች በታሪክ ዘመናቸው ውስጥ ስህተትን ሠርተዋል። እግዚአብሔር የመራጣቸው ፍጹም ስለሆኑ አይደለም። ነገር ግን ነገር ግን እርሱ በእኛ ውስጥ ጠንካራ እንደሆነ ሊያሳየኝ ይችላል። እርሱ በእውነት በዓላማ የዚህን ዓላም ደካማና ሞኝ ነገር በመምረጥ እያንዳንዱን ለማስደነቅና ታላቅነቱን አሳየ (1ኛቆሮ. 1፡28-19)። ከጠላት ፍጹም ሁን የሚልንና ፈጽሞ ስህተት አትሠራም የሚለውን ግፊት አትቀበል።በእያንዳንዱ ቀናት የተቻለህን ሁሉ አድርግና የቀረውን ሥራ ለመሥራት በእግዚአብሔር ታመን። በሠራኸው ስህተት ፈጽሞ አትፈር፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ከስህተቶችህ የመማር አመለካከት ይኑርህ። በድጋሚ ያንን ስህተት ላለማድረግ የምትሠራውን ስህተቶች አንደ ኮሌጅ የትምህርት ኮርስ በመቁጠር ተቀበላቸው።
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ አትፍር እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው።