እውነተኛ ጠላታችሁ ማነው?

እውነተኛ ጠላታችሁ ማነው?

ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ከሥልጣናትና ከኃይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው፡፡ – ኤፌ  6፡12

አስቸጋሪ ሁኔታዎችን እያጋጠማቹ ነው?በሆነ የህይወታችሁ አቅጣጫ አቅራቦት አስፈልጓችሁ ከየት እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን አቅቷችኋል?ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች በጣም ከባድ ችግሮችን እያሳለፉ ነው፡፡አንዳንዶች ስራቸውን እና ጥቅማ ጥቅሞቻቸውን አጥተዋል፡፡ሌሎች ደግሞ ከከባድ የጤና ችግር ጋር እየታገሉ እንደ መጠለያ፣ምግብ እና ልብስ ካሉ ከመሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው በተጨማሪ በቋሚነት የመድሀኒት እና የህክምና ወጪያቸውን እንዴት እንደሚሸፍኑ ማሰብ ላይ ናቸው፡፡

የሚያስፈራሩን ብዙ ነገሮች በአለም ውስጥ አሉ፡፡ዋናው ጠላታችን-ፍርሀት-ግን እዛ የለም፡፡

ኤፌ.6፡12 ጦርነታችን ከስጋ እና ከደም ጋር አይደለም ነገር ግን ከነፍሳችን ጠላት ጋር ነው ብሎ ያስታውሰናል፡፡በጦርነታችን ውስጥ ስለጠላታችን ማንነት ግራ መጋባት አያስፈልግም፡፡

የማይታየው አምላካችን የማይታየውን ጠላታችንን ለማሸነፍ ከበቂም በላይ መሆኑ የምስጋና ምክንያታችን ነው፡፡እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ፍቅር በጥልቀት ወደ መረዳት ስንመጣ  እኛን የሚመለከተንን ማናቸውንም ነገር ሁልጊዜም እንደሚያስተካክልልን ይገባናል፡፡

የማይታየውን ጠላታችሁን መፍራት የለባችሁም፡፡የጨለማውን መንፈሳዊ ሀይላት በብቸኝነት ማሸነፍ በሚችለው በእግዚአብሔር እመኑ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ እውነተኛው ጠላቴ ማን እንደሆነ  እና አንተ ደግሞ እጅግ ሀይለኛ እንደሆንክ እንድረሳ አትፍቀድልኝ፡፡ጠላት ወደ ህይወቴ የሚወረውረውን እያንዳንዱን ነገር እንደማልችለው አውቃለሁ፣አንተ ግን ትችለዋለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon