ከበቂ በላይ

ከበቂ በላይ

ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል። – ት.ኢሳ 53:11

ብዙዎቻችን ትልቁ ችግር ራሳችንን አለመዉደዳችን ነዉ፡፡ ደግሞም የተጎዳዉና የተሳሳተ መረጃ የሚሰጠዉ ዉጫዊ ገጽታችን እርግጥ እግዚአብሔር ሊወደን ይችላል ብሎ ማመንን ከባድ አድርጎብናል፡፡

ከእንደዚህ ዓይነት ችግር ጋር ለዓመታት ታግያአለሁ፡፡ በትንሹ የጊዜዬን 75 በመቶ ራሴን ለመቀየር ስሞክር ነበር ነገር ግን ዲያብሎስ ጥፋተኝነት እንዲሰማኝ ባደረገ ቁጥር ራሴን አስጨንቅ ነበር፡፡ ጥሩ እንደሆንኩ ፈጽሞ አስቤ አላዉቅም፡፡

ኢሳ 53 የሚነግረን ኢየሱስ ስለ ኀጢአታችን እንደሞተና በደላችንን እንደተሸከመ ነዉ፡፡ እጅግ ስለደወወን በሀጥያት ኩነኔ እንዳንሰቃይ የዕዳችንን ዋጋ ከፍሎልናል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከልብ ብንቀርብና ይቅር እንዲለን ብንጠይቀዉ ይቅር ይለናል ስለዚህ በኩነኔ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

እግዚአብሔር ይወዳችኋል ይህንን እንድታዉቁና ዘወትር እንድትቀበሉ ይፈልጋል፡፡ ደግሞም ከክስና ኩነኔ ነጻ እንድትሆኑ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እያላችሁ ነዉ “እናንተ መልካም ናችሁ” ይህንን ተቀበሉና የድል ሕይወት ኑሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ልጅህ በደሌንና ቅጣቴን ወስዶታል፡፡ እኔ በክርስቶስ መልካም ነኝ፡፡ ዛሬ ይህንን አምኙ በበደለኝነት ስሜትና በኩነኔ መኖርን እቃወማለሁ፡፡ ስለ ኀጥአቴ ይቅርታ እጠይቅሃለሁ እቀበላለሁም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon