ከጳዉሎስ ጸሎቶች መማር

ከጳዉሎስ ጸሎቶች መማር

የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። (ኤፌሶን 1:17)

ዛሬ ጳዉሎስ የጸለየባቸዉ ጸሎቶች ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ፡፡ በኤፌሶን፣ በፊሊጲስዩስ፣ እና ቆላስይስ ዉስጥ ያሉትን ጸሎቶቹን ሳነብ፣ ስለምጸልያቸዉ ስጋዊ ጸሎቶቼ አፍራለሁ፣ የጳዉሎስ ጸሎቶች በህይወቴ ላይ አሉታዊ የሆነ ተጽእኖ ስለፈጠረብኝ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የጸሎት ህይወቴ እነደበፊቱ አይደለም፡፡ ጳዉሎስ ሰዎች ከተለያዩ ችግሮች ወጥተዉና ጥሩ ህይወት እንዲኖሩ አላየሁም፡፡ ከዚያ ይልቅ
በሚገጥማቸዉ ሁሉ ቁጡ እንዳይሆኑ፣ ከዚያ ይልቅ ታጋሾች፣ ጽኑ እንዲሆኑና ለሌሎች የእግዚአብሔር ጸጋ ምሳሌ የሆነ ኑሮ እንዲኖሩ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር አስፈላጊ ስለሆኑት ጉዳዮች ነበር የጸለየዉ እናም ከዚህ ልምምድ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገዉእኛም በዚህ መንገድ ስንጸልይእግዚአብሔር በህይወታችን

አስደናቂ ኃይሉን ያፈስልናል፡፡ ስለምንፈልጋቸዉ ሁሉ ነገሮች ከመጸለይ ይልቅ ስለመንፈሳዊ ህይወታችን የበለጠ መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡
የዛሬዉ ቃል ከጳዉሎስ መልክቶች መካከል ስለአንዱ ነዉ፡፡ ይህ ቃል የሚያስተምረንም ለጥበብና መገለጥ መጸለይ አንዱና ተቀዳሚ ጸሎታችን መሆን እንዳለበት ነዉ፡፡ ብርግጥ፣ ለጥበብና መገለጥ
እግዚአብሔርን መጠየቅ ከምንጸልይባቸዉ ጸሎቶች ሁሉ አስፈላጊዉ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ መገለጥ ማለት “መግለጥ፣” ሲሆን እኛም በክርስቶስ የተነሳ የኛ ስለሆኑት ነገሮች እግዚአብሔር እንዲገልጥልን መጠየቅ ይኖረብናል፡፡እሱ የቃሉን እዉነት ለእኛ እንዲገልጥና እንዲያሳየን መጠየቅ ይኖርብናል፤ ከዚህም የተነሳ እንዴት ላራሰችንና ለሌሎች መጸለይ እንደሚገባን እንረዳለን፡፡ አንድ ሰዉ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ህግጋቶች ወይም ስለ መንፈሳዊ እዉነት ሲነግረን፣ አጭር የሆነ መረጃ ነዉ፡፡ ነገርግን እግዚአብሔር እንድትረዱት ሲያደርጋችሁ፣ መገለጥ ይሆናል፤ መገለጠ ማለት ደግሞ የአንድን ነገር እዉነተኛነት እዉን የሚያደርግ ከኛ ሊወሰድ የማይችል ነዉ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ አግዚአበሔርን ስለተለያዩ ነገሮች መለመን ትተህ በምትኩ የሱ ህልዉና የበለጠ በህይወትህ እንዲኖር ጠይቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon