የእርሱ የመኖሪያ ሥፍራ

« …የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?» (1ኛቆሮ.3፡16)።

እኔ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በመሆን የሚገኘውን ታላቅ በረከት በመደነቅና በመፍራት ውስጥ ሆኜ አስባለሁ። እርሱ ትልቅ ነገር እንድሠራ ያነሳሳኛል፤ይመራኛል። በሁሉም ሥራችን ውስጥ በኃይል ያለብሰናል። እርሱ ከእኛ ጋር ህብረት በማድረግ ከእኛ ጋር ይኖራል፣ ፈጽሞ አይተወንም፣ አይረሳንም።

ይህንን አስብ እኔና አንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መኖሪያ እንሆናልን። ይህን እውነት በህይወታችን ውስጥ የግል መገለት እስኪሆንልን ድረስ ደጋግመን ደጋግመን ማሰላሰል ይጠበቅብናል። ይህንን ካደረግን እኛ ፈጽሞ ተስፋ ቢሶች፣ እርዳታ የለሾች፣ ሃይል የሌላቸው አንሆንም፤ እርሱ ከእኛ ጋር ሊሆን በሰጠን ተስፋ መሠረት ይናገረናል፣ ያደረታናል፣ ኃይልን ይሞላናል። እኛ ፈጽሞ ወዳጅ የሌለንና የምንሄድበት የማናውቅ አንሆንም፤ እርሱ በሰጠን ተስፋ መሠረትይመራናል፣ በምናደርገው ነገር ሁሉ ውስጥ አብሮን ይጓዛል።

ጳውሎስ ለወጣቱ ደቀመዝሙሩ ለጢሞቴዎስ ሲጽፍ « … በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር አድርገህ፥ ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ፤ መልካሙን አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ» (2ኛጢሞ.1።13 – 14)። ስለመንፈስ ቅዱስ የምታውቀው እውነት ሁሉ እጅግ የከበረ ነው። እናም ይህንን እውነት እንድትጠብቃቸውና በልብህ ውስጥ እንድታኖራቸው አበረታታሃለሁ። አነርሱ ከአንተ ሳታስበው አትፍቀድላቸው።ምክንያቱም አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመንክ አማኝ ነህና። መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ ሆኖ ስለእርሱ የምታውቀውን ሊያጎለብትልህ ብቻ ሳይሆን ሊመራህም በውስትህ አለ። ነገር ግን እንድታድግ እንዲረዳህና ለሌሎች ለማካፈል ይረዳሃል። አድረንቀው፣ አክብረው፣ ውደደውና አወድሰው። እርሱ በጣም መልካም፣ እጅግ ቸር፣ አስፈሪ ነው። እርሱ አስደናቂ ነውና አንተ የእርሱ የመኖራ ሥፍራ ነህ።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ በቀኑ ውስጥ ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለብዙ ጊዜያት ደጋግመህ እንዲህ በል «እኔ የእግዚአብሔር የመኖራ ሥፍራ ነኝ፤ እርሱ መኖራውን በእኔ ውስት አድርጓል»።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon