ይህ መንገድ የተሻለ ነው

« …እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ» (ዮሐ.16፡7)።

በህይወታችን ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ህልውና እና መገመት ከምንችለው ባሻገር አስደናቂና ነው። እርሱ አጽናኛችንና ይህ ማለት እርሱ የሚረዳንና በህይወት በምንመላለስበት የህይወት ጉዞበተጎዳንበት ነገር ሁሉ የሚያጽናናን ነው። መንፈስ ቅዱስ ከቀጣዩ እስትንፋሴ ይልቅ ለእኔ ቅርቤ እንደሆነ እንዳስብ

መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በህይወታችን ወዳለው የራሱ ዕቅድ ይመራናል እንዲሁም መመሪያ ይሰጠናል። የእርሱን አመራር አውቆ መጠቀም እውነተኛ የህይወት ጉዞ ነው። እኛ በራሳችን ሃሳብ፣ ስሜትና ፍላጎት መኖርን እንደ ልማድ (ባህል) አድርገነዋል፤ ነገር ግን እንደ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት መማር ያስፈልገናል። ኢየሱስ ወደ ሰውነት የመጣው እኛ በህይወት ዘመናችን የምንጓዝበትን ለመረዳት ነው። ኢየሱስ ይረዳናል ብሎ ኣሰቡ መሄድ ለእኛ ትልቅ መጽናናትን የሚሰጠን ይሆናል። እርሱ ታጋሽና እኛ ከእርሱ ለመማር እንስፈቀድን ድረስ እርሱ ከእኛ ጋር በቀጣይነት የሚሠራ ነው።

ኢየሱስ እርሱ ቢሄድና መንፈስ ቅዱስን ቢልክ የጠሻለ እንደሆነ ለምን መናገር አስፈለገው? ኢየሱስ በሥጋ በምድር ላይ ከመሆን ይልቅ የተሻለ ሊያደርገው የሚያስችል ምንድነው? ኢየሱስ በሥጋ በነበረበት ጊዜ በአንድ ጊዜ በአንድ ሥፍራ ብቻ ይገኝ ነበር። ይህ አስደናቂ ነው። እርሱ ፈጽሞ፤ ለአንድ አፍታ እንኳን አይተወንም። እርሱ ስለእኛ ሁሉንም ነገር ያውቃል፤ እንዲሁም በህይወታችን ያለውን የተሰበረ ወይም የቆሰለ ማንነታችንን ሊፈውስ እየሠራ ይገኛል፤ እንዲሁም ሁሉንም ወደ ትክክለኛው የሥራው ሥርዓት ለመመለስ ይሠራል። በአስደናቂው የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ጥበብ ሁልጊዜ (በእያንዳንዱ ቀናት) በሁሉም መንገዶች የተሻለና የበለጠ ነገሮችን እናገኛለን።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ መንፈስ ቅዱስ አሁን አንተ የሆንከውን ተቀብሎና እርሱ እንድትሆን የሚፈልገውን ሰው አድርጎ እንዲሠራህ ለምነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon