ለምን ጌታ ሆይ?

ግራ ተጋብታችኋል? አንድ እንግዳ ነገር፣ ፈጽሞ ሊገባችሁ ያልቻለ ጉዳይ በህይወታችሁ ሳትፈልጉት እየሆነባችሁ ይሆን? ምናልባት የነገሩ ምክንያት ከዚህ ቀደም በአንድ የህይወት አጋጣሚያችሁ ውስጥ ሳይገባችሁ ያለፈ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህ የተነሳ ‹‹ጌታ ሆይ ምነው እንዲህ ያሉ ነገሮች በእኔ ላይ ? … ምነው እንዲህና እንዲያ ሆነው ቢያልፉ ኖሮ? አባት ሆይ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በእኔ ህይወት ውስጥ ለምን እንዳለፉ ሚስጠሩ አልገባኝም ›› እያላችሁ ትናገሩ ይሆናል፡፡ ልዩ ልዩ ግራ መጋባቶች በብዙ ሠዎች ህይወት ውስጥ እንደሚያልፉ ማስተዋል ከጀመርሁ ቆይቻለሁ፡፡ እኔም ከዚህ በፊት እንዲህ ባለው ግራ የመጋባት ህይወት ውስጥ ማለፌን አስታውሳለሁ፡፡ ያም ብቻ አይደለም ግራ መጋባት በሌሎች ሠዎች ላይም የሚያደርሰውን ከፍተኛ ስቃይ በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡ከዚህ የተነሳ ሠዎች ግራ ከመጋባት ህይወት ውስጥ የሚወጡበትንና ደግሞ ግራ መጋባት እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ደጋግሞ አስቤበታለሁ፡፡

አውርድ
ለምን ጌታ ሆይ?
Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon